የሰላም ሥምምነቱን እናበረታታለን፤ ለቁርጠኛ አፈፃፀሙም ጥሪ እናቀርባለን!   

ሥማችንን ከዚህ በታች ያኖርን የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ (ኢፌዴሪ) መንግሥት እና ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) ጦርነቱን በዘላቂነት ለማቆምና ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን በተሟላ መልኩ ለማስከበር መሥማማታቸውን ከልብ እናደንቃለን። ይህ ሥምምነት በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል ለሁለት ዓመታት በዘለቀው ጦርነት ለተጎዱ መላ ኢትዮጵያውያን ትልቅ ትርጉም እንዳለው እናምናለን። ሁለቱም ወገኖች ልዩነታቸውን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ቁርጠኛ ሆነው በዘላቂነት […]

Read More

ካርድ በግል መረጃ ጥበቃ ረቂቅ አዋጅ ላይ የማሻሻያ ጥቆማዎችን አቀረበ

የመብቶችና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል (ካርድ) በኢትዮጵያ የግል መረጃ ጥበቃ ረቂቅ አዋጅ ያሉበትን ክፍሎችን በመለየት ሕጉ ፀድቆ ከመውጣቱ በፊት ትኩረት እንዲደረግባቸው የማሻሻያ ሐሳቦችን አቀረበ። በመጀመሪያ በ2012 በሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተዘጋጅቶ በኋላ በ2013 የተሻሻለው ረቂቅ አዋጅ የግል መረጃን ጥቅም በመገንዘብ ጥበቃ ሊደረግለት እንደሚገባ ያወሳል፡፡ ይሁን እንጂ ረቂቅ ሕጉ ያለመውን የግል መረጃ ጥበቃ ውጤታማ በሆነ መንገድ ለመጠበቅ ማሻሻያ […]

Read More

35 አገር በቀል የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች የሰላም ጥሪ እንዳያቀርቡ መከልከላቸውን አወገዙ

ጳጉሜ 1 ቀን 2014 በኢንተር ለግዠሪ ሆቴል “አስቸኳይ የሰላም ጥሪ” ለማቅረብ ዝግጅት አድርገው ጋዜጣዊ መግለጫ ሊሰጡ የነበሩ አገር በቀል የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች “ከመንግሥት አካል የመጣን ነን” ባሉ ሲቪልና የፖሊስ የደንብ ልብስ በለበሱ ሰዎች መግለጫ እንዳይሰጡ መከልከላቸውን አወገዙ፡፡ ድርጅቶቹ ማክሰኞ በተመሳሳይ ቀን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ ይህ ክልከላ የሲቪክ ምኅዳሩን የሚያጠብ እንደሆነና ከላይኛው የመንግሥት አካላት ይቅርታ ሊጠየቅበት […]

Read More

አስቸኳይ የሰላም ጥሪ!

በቅድሚያ ይህንን የሰላም ጥሪ ጋዜጠኞች በተሰበሰቡበት ለማድረግ ዛሬ ጠዋት አቅደን የነበረ ቢሆንም፣ ማንነታቸውን ያልገለጹ ነገር ግን የመንግሥት አካል ነን ያሉ ግለሰቦች፣ ባልተገለጸ ምክንያት ጋዜጣዊ መግለጫውን መስጠት እንደማይፈቀድልን ነግረውን አስተጓጉለውብናል። ይህንን ክልከላ ያዘዘው አካል ማን እንደሆነ ብንጠይቅም መልስ አላገኘንም። የዚህ መግለጫ አዘጋጅ አገር በቀል ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች እስከምናውቀው ድረስ፣ ለመንግሥት የፀጥታ አካላት ቅድሚያ ማሳወቅ የሚጠይቁት የአደባባይ […]

Read More

ካርድ ከዳታ ፎር ቼንጅ ጋር በመተባበር የሁለት ሳምንታት የበይነመረብ ዘመቻ በበይነመረብ ተዳራሽነት ላይ ማድረግ ጀመረ

የመብቶች እና  ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል (ካርድ) በ“ዳታ ፎር ቼንጅ” የውሂብ ትንታኔ (ዳታ አናሊሲስ) ፌሎሺፕ እና የውሂብ-ተረክ (ዳታ ስቶሪ) ዝግጅት አቅም ማሳደጊያ ድጋፍ በመቀበል በበይነመረብ ላይ የሚካሔድ እና ለሁለት ሳምንታት የሚቆይ የበይነመረብ ተዳራሽነትን መስፋፋት የሚጠይቅ ዘመቻ፣ በበይነመረብ ላይ ጀመረ። የበይነመረብ ዘመቻው “የዲጂታል ክፍፍል፤ የበይነመረብ ተዳራሽነት መጓደል የኢትዮጵያ አቅም ላይ የጣለው እንቅፋት” በሚል ርዕስ የሚደረግ ሲሆን፥ በመረጃ […]

Read More