በእስር ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞችንና ጦማሪዎችን በዓለም ፕሬስ ነጻነት ቀን እናስታውሳቸው


የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ በወሰነው መሰረት በየዓመቱ ሜይ 03 የዓለም ፕሬስ ነጻነት ቀን በመላው ዓለም ተከብሮ ይውላል፡፡ የቀኑ መከበር ዋና ዋና አላማዎች የፕሬስ ነጻነት መርሆዎችን ለማስተዋወቅና ለማጉላት፣ በዓለም ዙሪያ የፕሬስ ነጻነት ትግበራን መገምገም፣ ሚዲያን ከጥቃት መከላከልና ገለልተኛነቱንና ነጻነቱን መጠበቅ እንዲሁም ለፕሬስ ነጻነት መከበር ዋጋ የሚከፍሉ ጋዜጠኞችን መዘከር ይጠቀሳሉ፡፡
ኢትዮጵያ የዚህ የፕሬስ ነጻነት ቀን መከበርን ውሳኔ ተቀብላ ቀኑን ታከብራለች፡፡ ቀኑን በማመልከት ሃሳብን በነጻነት መግለጽ አገራችን ያለበትን ደረጃ ማስታወስ አስፈላጊ ነው፡፡ የዘንድሮው የፕሬስ ነጻነት ቀን በሚከበርበት በዚህ ወቅት እንኳ በእስር ላይ የሚገኙት ጋዜጠኞችና ጦማሪዎች ትንሽ የማይባሉ ናቸው፡፡
ዛሬ ሜይ 03-2017 የዓለም ፕሬስ ነጻነት ቀን ሲከበር፣ ሀሳባቸውን በነጻነት በመግለጻቸው ምክንያት በኢትዮጵያ መንግስት ለእስር ተዳርገው ቀኑን በእስር ቤት ሆነው የሚያሳልፉ ጋዜጠኞችንና ጦማሪዎችን እንዲህ ስማቸውን በማንሳት ለማስታወስ እንወዳለን፡፡
1 ጋዜጤኛና ጦማሪ እስክንድር ነጋ
2 ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ
3 ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ
4 ጋዜጠኛ ጌታቸው ሺፈራው
5 ጋዜጠኛ ዳርሰማ ሶሪ
6 ጋዜጠኛ ካሊድ ሞሃመድ
7 ጋዜጠኛ ጌታቸው ወርቁ
8 ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ
9 ጦማሪ ዘላለም ወርቃገኘሁ
10 ኢንተርኔት አክቲቪስት ዮናታን ተስፋዬ
እነዚህ ጋዜጠኞችና ጦማሪዎች በእስር ላይ የሚገኙ ናቸው፡፡ ከእነዚህ በተጨማሪ ደግሞ ሀሳባቸውን በነጻነት በመግለጻቸው ክስ ተመስርቶባቸው፣ ነገር ግን ከእስር ውጭ ሆነው ክሳቸው በይደር ያለ ጦማርያንና ጋዜጠኞች ይገኛሉ፡፡

እነዚህም፡-
1 በፍቃዱ ኃይሉ
2 ናትናኤል ፈለቀ
3 አጥናፍ ብርሃኔ
4 ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ
5 አምደኛ አምሳሉ ገ/ኪዳን

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *