በእነ እስክንድር ነጋ መዝገብ ምስክር እንዳይደመጥ በጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት እግድ ተጣለ

ሐምሌ 14፣ 2013፤ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ የፀረ ሽብረ እና የሕገ መንግሥት ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ጉዳዩን ያሳደረው የዐቃቤ ሕግ ምስክሮች እንዲያቀርብ ቢሆንም እንኳን ከጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በቀረበው የግድ ትዕዛዝ መሠረት፣ የዐቃቤ ሕግ ይግባኝ ተቀባይነት በማስገኘቱ ሰበር ሰሚው ችሎት ጉዳዩ ያስቀርባል ተብሎ ስለታመነበት  ለሐምሌ 26፣ በሬጅስትራር በኩል ተከሳሾች የመልስ መልስ እንዲያስገቡ እና እስከዛው ድረስ በከፍተኛ ፍርድ ቤት ያለው ሒደት ለግዜው እንዲታገድ ትዕዛዝ ሰቷል።

ተከላካይ ጠበቆች በቀረበው ትዕዛዝ ላይ የትዕዛዙ ላይ ክብ መሐተብ ባለመኖሩ ትዕዛዙ ተቀባይነት ሊኖረው እንደማይገባ  እና ችሎቱ ዐቃቤ ሕግ ምስክር ማቅረብ እንዳልፈለገ ተቆጥሮ መዝገቡ ተቋርጦ ተከሳሾች በውጪ እንዲቆዩ፣ ነገር ግን ችሎቱ ትዕዛዙን የሚቀበለው እንኳን ቢሆን ተከሳሾች እስከዛው ቀን ድረስ በምን ሁኔታ ይቆዩ የሚለው ላይ ሰበር ሰሚው ምንም ትዕዛዝ ስላልሰጠበት ይህ ችሎት መሠረታዊ መብታቸውን ሊጠብቅላቸው ይገባል ሲሉ ተከራክረዋል።

ዐቃቤ ሕግ በበኩሉ ማሕተም በሚመለከት በተቀሩን የቀጠሮ ቀናቶች ድረስ አስተካክለን እናቀርባል በማለት የቀጠሮውን ቀን በሚመለከት ግን በቀረበው ትዕዛዝ መሠረት ቀጠሮ ይሰጠን ሲሉ ችሎቱን ጠይቀዋል። ፍርድ ቤቱ የትዕዛዙን ተዓማኒነት ለማረጋገጥ ዐቃቤ ሕግ እስከ ዛሬ ዘጠኝ ሰዓት ድረስ ክብ ማሕተም አስደርጎ እንዲያቀርብ፣ የተከሳሾችን ሁኔታ እና የቀጠሮ ቀን በሚመለከት ዐቃቤ ኽግ ካመጣው መልስ በኋላ በደብዳቤ ለማረሚያ ቤቱ የምናሳውቅ ይሆናል ብለዋል።

ከዚህ ቀደም የነበሩትን የምስክር አሰማም ክርክሮች እዚህ ያገኛሉ

ዐቃቤ ሕግ ያቀረበው የእግድ ደብዳቤ ከታች የተመለከተው ነው።

Center for Advancement of Rights and Democracy (CARD)

Making Democracy the Only Rule of Game!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *