አስቸኳይ ክፍት የሥራ ቦታ ማስታወቂያ

የመብቶችና ዴሞክራሲ ብልፅግና ማዕከል – ካርድ (በቀድሞ መጠሪያው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ፕሮጀክት – ኢሰመፕ) መንግሥታዊ ያልሆነ፣ በሰብኣዊ እና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ላይ የሚሠራ፣ በሲቪል ማኅበራት ድርጅቶች ኤጀንሲ ምዝገባ ቁጥር 4307 የተመዘገበ ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ ተፈጥራ ማየትን ራዕይ አድርጎ የሰነቀ ድርጅት ነው። ካርድ ለሚያከውናቸው የተለያዩ ከመብቶች መከበር እና የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ አጋዥ ሥራዎች ጋር የተያያዙ የሒሳብ ሥራዎችን የምታከናውን/የሚያከናውን ባለሙያ (አካውንታንት) አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።

የሥራ መደቡ መጠሪያ – አካውንታንት

ዋና ዋና የሥራ ኀላፊነቶች

 • ዓለም ዐቀፍ ደረጃን የጠበቀ የሒሳብ አያያዝ ስርዓት መዘርጋት፣
 • ካርድ/ድርጅቱ የሚጠቀምበትን የሒሳብ አያያዝ ሶፍትዌር መወሰንና ጥቅም ላይ ማዋል፣
 • የሒሳብ አያያዝ ስርዓቱ የሚስፈልጋቸውን የሒሳብ መዛግብት መለየት፣ ማዘጋጀት፣ ማሳተምና ጥቅም ላይ እንዲውሉ ማደረግ፣
 • የዕለት ሒሳብ ወጪ አያያዝን መዘገብ፣ መቆጣጠር፣
 • ዕለታዊ፣ ወርሐዊ፣ የሦስት ወራትና፣ የስድስት ወር እንዲሁም ዓመታዊ ሪፓርቶችን ማዘጋጀት
 • የሒሳብ ሪፖርት ደጋፊ ሰነዶች በአግባቡ መዘጋጀታቸውን እና መያዛቸውን ማረጋገጥ፣
 • የባንክ ሒሳቦችን እና ቼኮችን በበላይነት መቆጣጠር፣ ወጪና ገቢን መያዝ፣
 • አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ የድርጅቱን ሒሳብ ነክ ሥራዎች ድጋፍ ከሚያደርጉ ድርጅቶች ጋር ድርጅቱን ወክሎ ግንኙነት ማድረግ፣
 • ለቦርድ አመራር እና ለድርጅቱ የፕሮግራም ሥራ አመራሮች የፕሮጄክት የፋይናንስ አፈፃፀም ላይ ሪፖርት ማቅረብ እና የፋይናንስ ዕቅዱ በታለመለት ጊዜ መጠናቀቁን መከታተል፣ ማረጋገጥ፣
 • አዲስ ለሚዘጋጁ ፕሮጄክቶች፣ ፕሮፖዛሎች የፋይናንስ ፕሮፓዛል ማዘጋጀት፣
 • ድርጅቱን ወክሎ ውል መፈፀም እና ሌሎች አስተዳደራዊ ሥራዎችን ማከናወን፣

ተፈላጊ ችሎታ

 • የሒሳብ አያያዝ እና የአስተዳደር ዕውቀት ያላት/ያለው፣
 • በሒሳብ አያያዝ /አካውንቲንግ/ የመጀመሪያ ዲግሪ ያላት/ያለው እና ቢያንስ በፕሮጀክት ሒሳብ ሥራ ላይ 3 ዓመት ልምድ ያላት/ያለው፣
 • የሒሳብ አያያዝ ሶፍትዌሮችን በሚገባ መጠቀም የምትችል/የሚችል፣
 • መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ወይም የፕሮጄክት ሒሳብ አያያዝ ልምድ ያላት/ያለው፣
 • የሒሳብ አሠራር ስታንዳርድና መርሖዎችን ጠንቅቃ/ጠንቅቆ የምታውቅ/የሚያውቅ እና በሚገባ የምትተገብር/የሚተገብር፣
 • መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ወይም የፕሮጄክት ሒሳብ አስተዳደር ልምድ ያላት/ያለው፣
 • የቢሮ አስተዳደር ሥራዎችንም ለመሥራት ፍቃደኛ የሆነች/የሆነ
 • አዲስ የሥራ ከባቢ ውስጥ የመሥራት፣ የማሳደግና ኀላፊነት የመውሰድ ዝግጁነት ያላት/ያለው፣
 • የሰብኣዊ መብቶች እና የዴሞክራሲ ግንባታ ሥራዎች ዙሪያ ለመሥራት ከፍተኛ ፍላጎት እና ተነሳሽነት ያላት/ያለው፣
 • በቂ እና ፈጣን የኮምፒውተር እና የኢሜል አጠቃቀም ልምድ ያላት/ያለው እና በማንኛውም አስቸኳይ ሁኔታ በኢንተርኔት አማካኝነት ሥራ የማፋጠን ችሎታ ያላት/ያለው፣

ደመወዝ – በስምምነት (ከ2 ዓመት ያላነሰ ልምድ፣ ለሰብአዊ እና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ሥራ ቁርጠኝነት መሠረት ያደረገ)

የማመልከቻ መንገድ
አመልካቶች – ሲቪ እና የማመልከቻ ደብዳቤ በካርድ ኢሜይል አድራሻ info@cardeth.org በማያያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት መስከረም 19/2011 ጀምሮ ባሉ 5 ተከታታይ ቀናት መላክ ይችላሉ። ለቃለ መጠይቅ የተመረጡ አመልካቾች ከመስከረም 24 በፊት በኢሜል እንዲያውቁ ይደረጋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.