አክቲቪስት ዮናታን ተስፋየ የይግባኝ አቤቱታ በሰበር ክርክሩን አሰምቷል (ጥቅምት 24/2010 )

ማህበራዊ ሚዲያ በተለይም ፌስ ቡክ ላይ በጻፋቸው ጽሁፎቹ ምክንያት የሽብር ወንጀል ፈጽመሃል በሚል የስድስት አመት ከስድስት ወር እስራት የተፈረደበት የሰማያዊ ፓርቲ የቀድሞው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አክቲቪስት ዮናታን ተስፋዬ ዛሬ ጥቅምት 24/2010 ዓ.ም የፌደራል ጠ//ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ወንጀል ችሎት የይግባኝ አቤቱታ ክርክር አሰምቷል፡፡

አቶ ዮናታን ተስፋዬ ይግባኝ አቤቱታ ያቀረበው በስር ፍርድ ቤት (ከ/ፍ/ቤት ልደታ 4ኛ ወንጀል ችሎት) ግንቦት 08/2009 ዓ.ም በተሰጠው የጥፋተኝነት ፍርድ እና ግንቦት 17/2009 ዓ.ም በተጣለበት የቅጣት ውሳኔ ላይ ቅር በመሰኘት መሆኑ ተመልክቷል፡፡

ይግባኝ ባይ አክቲቪስት ዮናታን ተስፋዬ የስር ፍ/ቤት ያስተላለፈበት የጥፋተኛነት ፍርድ ተሸሮ በነጻ እንዲሰናበት፣ ይህ የማይሆን ከሆነም እስካሁን በእስር የቆየው ጊዜ በቂ ተብሎ ከእስር እንዲለቀቅ እንዲታዘዝለት በአቤቱታው ላይ ጠይቋል፡፡ ይግባኝ ባይ የይግባኝ አቤቱታውን በጽሁፍ ለይግባኝ ሰሚ ችሎቱ ያስገባ ሲሆን፣ በዛሬው ውሎ መልስ ሰጭ ፌ/አ/ህግ መልስ ሰጥቷል፡፡

አቶ ዮናታን ተስፋዬ በእስር ከሚገኝበት ዝዋይ ፌደራል ማረሚያ ቤት ሆኖ በፕላዝማ ጉዳዩን ተከታትሏል፡፡ ይግባኝ ሰሚ ችሎቱ በክርክሩ ላይ ብይን ለማሰማት ለህዳር 18/2010 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

 

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *