ፍርድ ቤቱ እነ ስብሓት ነጋ ‘ዳኛው ከቀዳሚ ምርመራ መዝገብ ይነሱልን’ ሲሉ ያቀረቡትን አቤቱታ ውድቅ አደረገ

መጋቢት 17፤ 2013 – በእነ ስብሓት ነጋ መዝገብ ሥር የተከሰሱት ተከሳሾች ከፕሮፌሰር ሰለሞን ኪዳኔ፣ አምባሳደር አባዲ ዘሙ፣ አምባሳደር አባይ ወልዱ እና ሙሉ ገብረ እግዚአብሔር ውጪ ያሉት ሁሉም ተከሳሾች በፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ላይ ቀርበዋል።

ተጠርጣሪዎች ከዚህ ቀደም ቅድመ ምርመራውን ሲመለከቱ የነበሩትን ዳኛ ከዚህ በኋላ ገለልተኛ ሆነው ሊመለከቱልን ስለማይችሉ ከመዝገቡ ይነሱልን ሲሉ ማመልከታቸው ይታወሳል።

ይሁንና ፍርድ ቤቱ እነስብሓት ነጋ ዳኛው በግዜ ቀጠሮ መዝገቡ ላይ ገለልተኛ ሆነው እንዳላዩላቸው የሚያሳይ ማስረጃ ሳያቀርቡ እንዲሁ በጭፍንነት ጥያቄ አቅርበዋል በማለት፣ ዳኛው የጊዜ ቀጠሮ ጉዳዩን ሲመለከቱ ገለልተኛ እና ፍትሓዊ ሆነው መዳኘታቸውን በተጨማሪም ካለምንም ጫና ጉዳያቸውን ሲመለከቱ እንደነበር መርምሮ ፍርድ ቤቱ ስላመነበት ጥያቄውን ውድቅ አድርጎታል።

በሌላ በኩል ተጠርጣሪዎቹ ከታሰሩበት ማረሚያ ቤት፣ ፍርድ ቤቱ ርቀት ስላለው እና ከነሱ የቁጥር ብዛት አሁን ካለው ወረርሽኝ አንፃር ችሎቱ ጠባብ ስለሆነ ወደ ልደታ ምድብ ችሎት ይቀየርልን ብለው ላቀረቡት አቤቱታ ፍርድ ቤቱ ጉዳዩ አስተዳደራዊ መሆኑን በማውሳት ክርክር የሚደረግበት ያለመሆኑን እና ጥያቄም መቅረብ ካለበትም ሥልጣን ላለው ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ማቅረብ ይቻላል በማለት ምላሽ ሰጥቷል።

ችሎቱ በቀጣይ የዐቃቤ ሕግ የቅድመ ምርመራ ምስክር ሒደቱን በሚመለከት ዳኛው ላይ በሌላ ዳኛ አስተያየት ተሰቶበት እስከሚቀርብ ድረስ በቀጣይ በጽሕፈት ቤት ቀጠሮ ይሰጣል ተብሏል።

እነስብሓት ነጋ መጋቢት 14 በዋለው ችሎት ‘ጉዳያችን በትግራይ ክልል ፍርድ ቤት ይታይልን’ ሲሉ አቤቱታ አቅርበው ውድቅ እንደተደረገባቸው ይታወሳል።

Center for Advancement of Rights and Democracy (CARD)

Making Democracy the Only Rule of Game!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *