እነ ጃዋር መሐመድ “የትግራይ ሕዝብ ላይ የሚደረገውን ግፍ በመቃወም” ለሁለት ቀን የረሀብ አድማ እንደሚያደርጉ አሳወቁ

  • ተከሳሾቹ ከሁለት ሦስት ዓመት ወዲህ ባሉ ቀጣይ የፍርድ ቤት ቀጠሮዎች መቅረብ እንደማይፈልጉ ተናግረዋል።

ግንቦት 18፣2013 - የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አንደኛ የፀረ ሽብር እና ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች ችሎት በጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ መሠረት ዐቃቤ ሕግ የምስክር ስጋት ናቸው ያላቸውን ጉዳዮች ዘርዝሮ ለግንቦት 30 በጽሕፈት ቤት በኩል ያቅርብ ብለዋል።

በመዝገቡ አራተኛ ተከሳሽ የሆኑት ሀምዛ ቦረና ከችሎቱ ፍቃድ ሳያገኙ በደንቢ ዶሎ ለተገደለው ልጅ የሕሊና ፀሎት እናድርግ በማለት ከተቀሩት 20 ተከሳሾች ጋር በመሆን ለ20 ሰከንድ የሕሊና ፀሎት አድርገዋል። ፍርድ ቤቱም ተገቢ ድርጊት አይደለም በማለት አልፎታል።

ጃዋር መሐመድ እና በቀለ ገርባ በበኩላቸው መንግሥት እኛን ሊለቀን ስለማይፈልግ፣ ቀጠሮ ከ2 ወይም 3 ዓመት በኋላ ይሰጠን በማለት፣ በትግራይ ሕዝብ ላይ የሚደረገው ግፍ ይቁም፣ ከዛሬ ጀምሮ አጋርነታችንን ለማሳየት ለሁለት ቀን የርሀብ አድማ እናደርጋለን ብለዋል።

ባለፈው የሕክምና ጥያቄ አንስተው ለነበሩ ተከሳሾች ማረሚያ ቤቱ ሕክምና እንዲያመቻችላቸው ችሎቱ ትዕዛዝ ሰጥተዋል።

ቀጣይ ቀጠሮ ለሰኔ 10፣ 2013 ተቀጥሯል።

Add a review

The comment language code.

Restricted HTML

  • Allowed HTML tags: <a href hreflang> <em> <strong> <cite> <blockquote cite> <code> <ul type> <ol start type> <li> <dl> <dt> <dd> <h2 id> <h3 id> <h4 id> <h5 id> <h6 id>
  • Lines and paragraphs break automatically.
  • Web page addresses and email addresses turn into links automatically.