ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት አቃቤ ህግ በእነ እስክንድር ነጋ መዝገብ ምስክር የማሰማት ሂደት ‘ከመጋረጃ ጀርባ’ ይሁንልኝን ጥያቄ ውድቅ አድርጓል።

የህዳር 29/2013 ዓ.ም የፍርድ ቤት ውሎ።

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የልደታ ምድብ ችሎት የእነ እስክንድር ነጋ የክስ መዝገብ  ህዳር 29 ቀን 2013 ዓ.ም እደሚከተለዉ ተመልክቶታል፡፡ በመዝገብ ስር ከተከሰሱት ዉስጥ እስክንድርን ጨምሮ አራት ተከሳሾች የቀረቡ ሲሆን ፤ ስድስተኛና ሰባተኛ ተከሳሾች በፖሊስ ቁጥጥር ስር ባለመዋላቸው ችሎት ላይ አልቀረቡም፡፡ ችሎቱ በዋናነት በሁለት ጉዳዮች ማለትም በባለፈው ችሎት በተከሳሾች ጠበቆች በኩል የቀረቡ የክስ መቃወሚያን እና በዐቃቤ ሕግ የቀረበው ምስክሮችን የመስማት ሂደት ላይ ብይን ሰጥቷል፡፡ የብይኑም ይዘት በፅሁፍ ቀርቦ በመሃል ዳኛው ተነበዋል፡፡

በዚህ መሰረት ችሎቱ በተከሳሾች ከቀረቡ መቃወሚያዎች ውስጥ ተከሳሾች በቀጥታ የሰው ህይወት ማጥፋታ ላይ መሳተፋቸውን የሚያሳይ ማስረጃ ዐቃቤ ሕግ አለመቅረቡን ፣ አንደኛና ሁለተኛ ተከሳሾች በስልጤ ሰፈር አንድን ብሔር በሌላ ብሕር እንዲነሳ አድርገዋል ለሚለው ክስ እና የክስ መደራረብ በተመለከተ የቀረቡት መቃወሚያ ችሎቱ ውድቅ አድርጎታል፡፡ በሌላ በኩል ከማህበራዊ ሚድያ አጠቃቀም በተመለከተ ለቀረበው ክስ በተከሳሾች የቀረበው መቃወሚያም ችሎቱ በመቀበል ለዐቃቢ ሕግ ጉዳዩን አጣርቶ በድጋሚ እንዲያቀርብ አዟል፡፡ እንዲሁም አራተኛ ተከሳሽ በተመለከተ በተለያዩ ክፍለ ከተማዎች ያሉ አባሎችና ወጣቶች በመጥራት ተልእኮ ሰጥተዋል የሚለውን ክስ በተመለከተ ዐቃቢ ሕግ አጣርቶ ዝርዝር ማስረጃ እንዲያቀርብ ተጠይቀዋል፡፡

በመቀጠል ችሎቱ የተመለከተው በእነ እስክንድር ነጋ የክስ መዝገብ ላይ ዐቃቤ ሕግ ምስክሮችን ከመጋረጃ ጀርባ ለማሰማት ያቀረበዉን ጥያቄ ነው፡፡ የምስክሮች የደህንነት ስጋት፣ ምስክሮች ከተከሳሾች የቅርብ ግኑኝነት እንዳላቸው እና ካሁን በፊት ማስፈራሪያ ስለደረሰባቸው ምስክሮችን ከመጋረጃ ጀርባ እንዲደመጡ በባለፈው ችሎት የቀረበው አቤቱታ በችሎቱ ተቀባይነት አላገኘም፡፡ በመሆኑም በዐቃቤ ሕግ የቀረበው የምስክር አሰማም ሂደት በተመለከተ አቤቱታው በማስረጃ ያልተረጋገጠ በመሆኑ ውድቅ ተደርገዋል፡፡

በችሎቱ ሂደት በአንድ በኩል ዐቃቤ ሕግ ስድስተኛና ሰባተኛ ተከሳሾች በተመለከት ከፖሊስ ጋር ተባበሮ ተከሳሶች ለማቅረብ ተለዋጭ ቀጠሮ ሲጠይቅ፤ በሌላ በኩል የሌሎች ተከሳሾች ጠበቆች የቀረበው ሀሳብ የፍትህ ሂደት ያዘገየዋል በማለት ተቃውመዋል፡፡ ችሎቱ ከተወያየ በሁላ የዐቃቤ ሕግ ጥያቄ ውድቅ አድርጎውታል፡፡ በመሆኑም በዚሁ መዝገብ ተከሰው በፖሊስ ቁጥጥር ስር ያልዋሉ ሁለት ተከሳሾች የሌሎች ተከሳሶች የተፋጠነ ፍትህ የማግኘት መብት እየጎዳ መሆኑን በመጥቀስም 6ኛ 7ኛ  ተከሳሾች በሚመለከት ፖሊስ መረጃ በሚያገኝ ግዜ ክስ የመመስረት መብት በመሰጠት ለግዜዉ ክሱ እዲቋረት ትፅዛዝ በመስጠት አቃቢ ህግ ክሱን አሻሽሎ እንዲቀርብ ለታህሳስ 13 ቀጣይ ቀነ ቀጠሮ ተሰጥቷል።

የችሎት ውሎ ማጠቃለያ ላይ አንደኛ ተከሳሽ አቶ እስክንድር  አቤቱታ አለኝ በማለት የመናገር እድል እንዲሰጣቸው ቢጠይቁም፤ ዳኛው ሃሳባቹ በፅሁፍ ማቅረብ ትችላላቹ በማለት ችሎቱ ተጠናቋል፡፡

Center for Advancement of Rights and Democracy (CARD)

Making Democracy the Only Rule of Game!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*

code