ካርድ በማኅበራዊ ሚዲያ ዘመን ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት እና ተግዳሮቶች ላይ ምክክር አካሔደ

ካርድ ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት በማኅበራዊ ሚዲያ ዘመን በሚል ርዕስ ከማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ጸሐፊዎች እና ጋዜጠኞች ጋር ታኅሣሥ 20 እና 21፣ 2013 የምክክር መድረክ አዘጋጅቶ ነበር። የምክክር መድረኮቹ በዌስተርን ፕላስ ሆቴል ለግማሽ ቀናት የተካሔዱ ሲሆን፣ ተፅዕኖ ፈጣሪ ጦማሪዎች እና ጋዜጠኞች ተድመውታል።

በምክክር መድረኮቹ ላይ ዶ/ር ወንድማገኝ ታደሰ ሙያዊ መግለጫቸውን የሕግ ማዕቀፎችን እና ዓለም ዐቀፍ እና አገር ዐቀፍ ዐውዶችን ባማከለ ሁኔታ ያቀረቡ ሲሆን፥ ይህንን ተከትሎ ጦማሪዎቹ እና ጋዜጠኞቹ የግል ተሞክሯቸውን እና ገጠመኛቸውን፣ እንዲሁም ተግዳሮቶቻቸውን ለተሳታፊዎቹ አጋርተዋል።

የምክክር መድረኮቹን ሙሉ ይዘት ከታች ይመልከቱ!

ሐሳብን የመግለግ ነጻነት በማኅበራዊ ሚዲያ ዘመን (ምክክር ከጦማሪዎች ጋር)
ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት በማኅበራዊ ሚዲያ ዘመን (ምክክር ከጋዜጠኞች ጋር)

Center for Advancement of Rights and Democracy (CARD)

Making Democracy the Only Rule of Game!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *