ካርድ ከዳታ ፎር ቼንጅ ጋር በመተባበር የሁለት ሳምንታት የበይነመረብ ዘመቻ በበይነመረብ ተዳራሽነት ላይ ማድረግ ጀመረ

የመብቶች እና  ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል (ካርድ) በ“ዳታ ፎር ቼንጅ” የውሂብ ትንታኔ (ዳታ አናሊሲስ) ፌሎሺፕ እና የውሂብ-ተረክ (ዳታ ስቶሪ) ዝግጅት አቅም ማሳደጊያ ድጋፍ በመቀበል በበይነመረብ ላይ የሚካሔድ እና ለሁለት ሳምንታት የሚቆይ የበይነመረብ ተዳራሽነትን መስፋፋት የሚጠይቅ ዘመቻ፣ በበይነመረብ ላይ ጀመረ።

የበይነመረብ ዘመቻው “የዲጂታል ክፍፍል፤ የበይነመረብ ተዳራሽነት መጓደል የኢትዮጵያ አቅም ላይ የጣለው እንቅፋት” በሚል ርዕስ የሚደረግ ሲሆን፥ በመረጃ ላይ የተመሠረተ በኢትዮጵያ ያለውን የዲጂታል ክፍፍል – ማለትም በበይነመረብ ተጠቃሚዎች እና ተጠቃሚ ያልሆኑ ዜጎች መካከል ያለውን ሁለገብ አቅምን ለመጠቀም ያላቸውን የዕድል ልዩነት – ያሳያል። ይህ ዘመቻ፣ በመሠረተ ልማት አለመስፋፋት፣ በዋጋ ውድነት፣ እና በመንግሥት ማዕቀብ ምክንያት የዲጂታል ክፍፍሉ ሰፊ መሆኑን እና ኢትዮጵያውያን በበይነመረብ ተዳራሽነት ከአፍሪካ አማካይ በታች መሆናቸውን በማሳየት ነገር ግን መንግሥት በዕቅዱ መሠረት ከሚያልመው ተቃራኒ መሆኑን ለማሳየት ያስችላል። የበይነመረብ አገልግሎት ዋጋ ተመጣጣኝ መሆን እና የተዳራሽነቱ መሥፋፋት ለሕዝቦች የነፍስ ወከፍ ገቢ መጨመር ይረዳል።

ዘመቻው በፌስቡክ፣ በትዊተር፣ በኢንስታግራም እና በቴሌግራም በአማርኛ፣ በእንግሊዝኛ እና በኦሮምኛ ይካሔዳል። ካርድ በበይነመረብ ተዳራሽነት አስፈላጊነት የሚያምኑ ግለሰቦችንም ይሁን ድርጅቶችን ዘመቻችንን #KeepItOn የሚል ሀሽታግ በመጠቀም እንዲቀላቀሉ እንጋብዛለን።  

የውሂብ-ተረካችንን እዚህ ያንብቡ!

Center for Advancement of Rights and Democracy (CARD)

Making Democracy the Only Rule of Game!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

*

code