የእነ እስክንድር ነጋ መዝገብ ለታህሳስ 16/ 2013 ተቀጠረ።

“ደጋፊዎቻችን በለበሱት የኢትዮጵያን ባንዲራ ምልክት ያለው ልብስና ማስክ ምክንያት ለሶስተኛ ግዜ ወደ ችሎት እንዳይገቡ በጸጥታ አስከባሪዎቸ ተክልክለውብናል” አቶ ስንታየው ቸኮል።

ቀን፡- 13/04/2013

ሰዓት፡- 4፡15

እነ እስክንድር ነጋ ባስገቡት የክስ መቃወሚያ ምክንያት አቃቤ ህግ ክስ አሻሽለህ አቅርብ በተባለው መሰረት የተሻሻለ ህግ ያቀረበ ቢሆንም ከችሎቱ ቀደም ብሎ ለፍርድ ቤቱ ማቅረብ ሲገባው ባለማቅረቡ ምክንያት ፍርድ ቤቱ ክሱ መሻሻል ወይም አለመሻሻሉን ግዜ ወስዶ ለመመርመር  እንዲያመቸው ቀጣዩን  ችሎት ለታህሳስ 16 ቀን 2013 ይዟል፡፡  ፍርድ ቤቱ በመቀጠል ተከሳሾችን አቤቱታ ካላቹ በጽሁፍ ማቅረብ ትችላላቹ በማለት አቅጣጫ የሰጠ ሲሆን፤ ተከሳሾችም አቤቱታቸው በችሎቱ እና በታዳሚው ፊት ለማቅረብ እንዲፈቀድላቸው ጠይቀዋል፡፡

አቶ እስክንድር ነጋም “ያለን ሁሉንም አቤቱታ በጽሁፍ ማቅረብ አንችልም፣ አቤቱታችን በችሎትና በታዳሚ ፊት የመሰማት መብታችን ይከበርልን፣ ጉዳያችን የህዝብ ስለሆነ ህዝቡ እንዲሰማልን ይሁን፣ ምርጫ እየደረሰብን ስለሆነ ለቀጣይ ቀጠሮ ያለቀለት አንድ አቋም ይዛቹ እንድትመጡ በትህትና እጠይቃለሁ’’ በማለት ሓሳቡን ገልጸዋል፡፡ በመቀጠል አቶ ስንታየሁ “ደጋፊዎቻችን በለበሱት የኢትዮጵያን ባንዲራ ምልክት ያለው ልብስና ማስክ ምክንያት ለሶስተኛ ግዜ ወደ ችሎት እንዳይገቡ በጸጥታ አስከባሪዎቸ ስለተከለከሉ ይህ ደግሞ የደጋፊዎቻችን መብት ስለሚጋፋ ደንብ አስከባሪዎች በህጉ መሰረት እንዲሰሩ ይደረግልን’’ በማለት ለችሎቱ አቤቱታ አቅርበዋል፡፡ በልላ በኩል ተከሳሽ አስካል ደምሴ ’”የጤና እክል ካጋጠመኝ ጀምሮ ስድስት ወር ሆኖኛል፣ በማረሚያ ቤቱ እየተደረገልኝ ያለው ክትትል በቂ ባለመሆኑ በግሌ ሙሉ ምርመራ አድርጌ እንድታከም ፍርድ ቤቱ ለማረሚያ ቤት ትእዛዝ እንዲሰጥልኝ’’፤ በተጨማሪም “ጠበቆቻችን ግዜ ስለማይበቃቸው ወንድና ሴት ተከሳሾች ለየብቻ ከማግኘት ይልቅ ክሳችን ተመሳሳይ ሰስለሆነ በአንድ ላይ እንዲያገኙን ይፈቀድልን’’ በማለት ጠይቃለች፡፡

በመጨረሻም ችሎቱ አለባበስና ማስክ በተመለተ ፍርድ ቤቱ ተወያይቶ በቀጣይ ችሎት ትእዛዝ እንደሚሰጥ፣ አስካል ድምሴ በግል እንድትታከም እና የማረሚያ ቤት አሰራር የሚፈቅድ ከሆነ ወንድና ሴት ተከሳሾች ጠበቆቻቸው በጋራ እንዲያገኙ ትእዛዝ በማስተላለፍ  ቀጣዩን  ችሎት ለታህሳስ 16 ቀን 2013 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥተዋል፡፡

Add a review

The comment language code.

Restricted HTML

  • Allowed HTML tags: <a href hreflang> <em> <strong> <cite> <blockquote cite> <code> <ul type> <ol start type> <li> <dl> <dt> <dd> <h2 id> <h3 id> <h4 id> <h5 id> <h6 id>
  • Lines and paragraphs break automatically.
  • Web page addresses and email addresses turn into links automatically.