የእነ እስክንድር ነጋ ይግባኝ ክርክር በፕላዝማ መበላሸት ምክንያት ሳይደመጥ ቀረ

ሚያዝያ 6፣ 2013፤ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ሁለተኛ ወንጀል ችሎት የምስክር አደማመጡ ላይ ክርክር ለማድመጥ ተሰይሞ የነበረ ቢሆንም በፕላዝማ መበላሸት ምክንያት ክርክሩን ሳያደምጥ ቀርትዋል።

የተከላካይ ጠበቆች በበኩላቸው እኛ ብንከራከርም ደንበኞቻቸው የራሳቸው መከራከሪያ ሐሳብ ስላላቸው እነሱ በሌሉበት መከራከር አንችልም በማለት ተመሳሳይ ችግር እንዳይገጥመን ተከሳሾች በአካል ቀርበው ክርክር ማድረግ እንዲችሉ ትዕዛዝ እንዲሰጥላቸው፤ በተጨማሪም  ደንበኞቻቸው የቀረበባቸውም ክስ ፖለቲካዊ ስለሆነ ችሎቱ መንግሥት ለሚፈልገው ዓላማ አስተዋፅዖ ባላደረገ መልኩ አጭር ቀጠሮ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።

ዐቃቤ ሕግ በበኩሉ ክሱ ፖለቲካዊ ነው የሚል እምነት እንደሌላቸው እና ወንጀል መሆኑንም ጠቅሰው ማቅረባቸውን በመግለጽ ተከላካይ ጠበቆች ያነሱትን ቅሬታ ተቃውመዋል። ፍርድ ቤቱ ተከሳሾችን በአካል አቅርበን ሠርተን አናቅውቅም፤ እነርሱን አቅርበን ሌሎች ተከሳሾችን አለማቅረብ ስለማንችል ለአሠራርም አመቺ ስላልሆነ ለሚያዝያ 15 በፕላዝማ ቀርበው ክርክር እንዲያደርጉ ሲል ውሳኔ ሰጥተዋል።

Center for Advancement of Rights and Democracy (CARD)

Making Democracy the Only Rule of Game!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *