የእነ ጃዋር መሐመድ መዝገብ ለተጨማሪ ክርክር ከጠቅላይ ፍርድ ቤት ወደ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተመለሰ

ግንቦት 11፤ 2013 - የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ሁለተኛ ወንጀል ችሎት በዐቃቤ ሕግ አቤቱታ ላይ ሁለቱንም ወገን አከራክሮ መዝገቡን መርምሮ ብይን  ለመስጠት ቀጠሮ ለዛሬ መሰጠቱ ይታወሳል።

ጃዋር መሐመድን ጨምሮ ሁሉም ተከሳሾች በጠበቆቻቸው ተወክለው ቀርበዋል።

ዐቃቤ ሕግ ፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የምስክር ሒደቱን በሚመለከት በግልጽ ችሎት እንዲሰማ ብሎ ውሳኔ ሰጥቶ የነበረውን ውሳኔ ይግባኝ በማለት ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት  ምስክሮችን በዝግ ችሎት እና ከማጋረጃ ጀርባ እንዲሰሙለት መጠየቁ የሚታወስ ነው።

ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ በሁለቱም ወገን የተነሱ ሐሳቦችን በማጤን እና የከፍተኛ ፍርድ ቤት የምስክሮቹ የሥም ዝርዝር እንዳይነገር (እንዳይታወቅ) የሚለውን ውሳኔ በማፅደቅ፣ ዐቃቤ ሕግ የምስክር ደኅንነት ጥበቃ አቤቱታ ላይ ለምስክሮቹ አስጊ ናቸው ያለውን ጉዳዮች በዝርዝር ለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በማቅረብ  በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክርክር  እንዲደረግበት ሲል ትዕዛዝ ሰጥተዋል። ቀጣዩ የከፍተኛ ፍርድ ቤት ክርክር ግንቦት 12፣ 2013 እንዲደመጥ ቀጠሮ ተይዞለታል።

Add a review

The comment language code.

Restricted HTML

  • Allowed HTML tags: <a href hreflang> <em> <strong> <cite> <blockquote cite> <code> <ul type> <ol start type> <li> <dl> <dt> <dd> <h2 id> <h3 id> <h4 id> <h5 id> <h6 id>
  • Lines and paragraphs break automatically.
  • Web page addresses and email addresses turn into links automatically.