የእነ ጃዋር መሐመድ ይግባኝ ክርክር በፕላዝማ መበላሸት ምክንያት ሳይካሔድ ቀረ

ሚያዝያ 6፣ 2013፤ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ የፀረ ሽብር እና የሕገ መንግሥት ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ባሳለፍነው ሳምንት የዐቃቢ ሕግ ምስክሮችን የመስማት ሐደቱ በግልጽ ችሎት እንዲሆን የሰጠውን ብይን ተከትሎ ዐቃቤ ሕግ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ማለቱ የሚታወስ ነው።

ተከላካይ ጠበቆች ምንም እንኳን ፕላዝማው ባይሠራም ዐቃቤ ሕግ መጥሪያ የደረሰን ሚያዝያ 5፣ 2013 ነው፤ ደንበኞቻችን ቀድሞ የደረሳቸው መጥሪያ የለም። ስለዚህ ከደንበኞቻችን ጋር የመዘጋጃ ግዜ ስላላገኘን ክርክር ማድረግ አንችልም ብለዋል።

በተጨማሪም በፕላዝማ መሆኑ የተከሳሾችን ፍትሕ የማግኘት ዕድል ስለሚያጣብብ በአካል ቀርበው መከራከር ቢችሉ ሲሉ አቤቱታ አስምተዋል። ፍርድ ቤቱ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ወደ አገር ውስጥ ከገባ ጀምሮ የፍርድ ቤቱ አሠራር በዚህ መልኩ መሆኑን እና በፕላዝማ መሆኑ የተከሳሾችን ዕድል ያጣብባል ብለው እንደማያምኑ፣ በፕላዝማ መሆኑ ተከሳሾች ሐሳባቸውን እንዳይገልጹ የሚያግዳቸው ነገር አይኖርም በማለት ተለዋጭ ቀነ ቀጠሮ ለሚያዝያ 15 ሰጥተዋል።

Add a review

The comment language code.

Restricted HTML

  • Allowed HTML tags: <a href hreflang> <em> <strong> <cite> <blockquote cite> <code> <ul type> <ol start type> <li> <dl> <dt> <dd> <h2 id> <h3 id> <h4 id> <h5 id> <h6 id>
  • Lines and paragraphs break automatically.
  • Web page addresses and email addresses turn into links automatically.