የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በእነ ጃዋር መሐመድ ላይ የዐቃቤ ሕግ ምስክሮች በግልጽ ችሎት እንዳይሰሙ አገደ

ሚያዝያ 1፣ 2013 - የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ የፀረ ሽብር እና የሕገ መንግሥት ጉዳዮች ወንጀል ችሎት የተከሳሾች መብትን የሚያጣብብ ስለሆነ ምስክሮች በዝግ ችሎት ሊሰሙ አይገባም በማለት፣ የዐቃቤ ሕግ በምስክር ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 699/2003 መሠረት 146 ምስክሮቼ በየደረጃው በዝግ ችሎት ‘ከመጋረጃ በስተጀርባ ምስክርነታቸው ይሰማልኝ’ ብሎ ያቀረበውን አቤቱታ ውድቅ ማድረጉ ይታወሳል። ይሁንና በውሳኔው ቅር የተሰኘው ዐቃቤ ሕግ ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ይግባኝ ብሏል። ችሎቱ የከፍተኛ ፍርድ ቤት ምስክሮች በግልጽ ችሎት እንዲሰሙ የሰጠውን ብይን ላይ እግድ በመጣል በጉዳዩ ላይ ክርክር እንዲያደርጉበት ለሚያዝያ 6 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

Add a review

The comment language code.

Restricted HTML

  • Allowed HTML tags: <a href hreflang> <em> <strong> <cite> <blockquote cite> <code> <ul type> <ol start type> <li> <dl> <dt> <dd> <h2 id> <h3 id> <h4 id> <h5 id> <h6 id>
  • Lines and paragraphs break automatically.
  • Web page addresses and email addresses turn into links automatically.