ፍርድ ቤቱ በእነ እስክንድር ነጋ መዝገብ ቀሪ 12 የዐቃቤ ሕግ ምስክሮችን እንዲታለፉ ትዕዛዝ ሰጠ

ታኅሣሥ 22፣ 2014 - የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ የፀረ ሽብርና ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች ወንጀል ችሎት በእነ እስክንድር ነጋ መዝገብ ቀሪ የዐቃቤ ሕግ ምስክርን በሚመለከት እንዲሁም ከኮሚሽኑ የመጣው ደብዳቤ ላይ ትዕዛዝ ለመስጠት ነው የቀጠረው።

ፍርድ ቤቱ በተደጋጋሚ ቀጠሮ ያልቀረቡበትን የዐቃቤ ሕግ ምስክር ፍፁም ከተማ በድጋሚ ተለዋጭ ቀጠሮ ሊሰጥ አይገባም ሲል ምስክርነታቸው እንዲታለፍ ብይን ሰጥቷል።

ዐቃቤ ሕግ ቀሪ 12 ምስክሮች ላይ ሐሳብ እንዲሰጥ ከፍርድ ቤቱ በተጠየቁት መሰረት፣ ማንነታቸው ሳይገለጽ ምስክርነታቸውን ይሰማልኝ ብዬ ያቀረብኩት ጥያቄ ፍርድ ቤቱ የማይቀበለው ከሆነ እስካሁን ባሰማኋቸው 6ምስክሮች ብቻ ብይን ይሰጥልኝ ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል።

ተከላካይ ጠበቆች በበኩላቸው በ12ቱ ምስክሮች ዙሪያ እስከሰበር ተከራክረን ግልጽ ውሳኔ የተሰጠበት ጉዳይ በመሆኑ ከዚህ በኋላ እንደገና የምናነሳው ነገር አይደለም ብለዋል።

ፍርድ ቤቱም ቀሪ 12ቱ ምስክሮች አሰማም በሚመለከት እስከ ሰበር ሰሚ ክርክር ተደርጎ ውሳኔ የተሰጠበት ጉዳይ በመሆኑ አልፈነዋል ብሏል።

ዐቃቤ ሕግ ከዚህ በፊት ከክስ ቻርጅ ጋር ባቀረቡበት የሰነድ ማስረጃ ላይ ተከላካይ ጠበቆች አስተያየት በጽሑፍ እናቅርብ ሲሉ የጠየቁ ሲሆን ፍርድ ቤቱም በጽሕፈት ቤት በኩል ማቅረብ እንደሚችሉ ገልጸዋል።

እስክንድር ነጋ በማረሚያ ቤት ደረሰብኝ ባሉት ድብደባ አጣርቶ አስተያየት እንዲሰጥ ታዞ የነበረው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ደረሰ የተባለውን ድብደባ በተመለከተ ከጥምቀት 12 ጀምሮ ምርመራ መጀመሩን ጠቅሶ በጥልቀት ለመመርመር ግን በጊዜ እጥረት ምክንያት እንዳልቻለ ለፍርድ ቤቱ በላከው ምላሽ አሳውቋል።

እስክንድር በበኩላቸው ኮሚሽኑ ካለው ተደራራቢ ሥራ አኳያ ቢታለፉ ችግር የለውም ዋናው ፖሊስ የያዘው ጉዳይ ነው ብለዋል።

ሌላው ምርመራውን እንዲያደርግ የታዘዘው የፌደራል ፖሊስ በበኩሉ ለፍርድ ቤቱ ባቀረበው ጽሑፍ እስክንድር ድብደባውን በፈፀመው ግለሰብ ክስ መመስረት እንደማይፈልጉ ነገር ግን ያስደበደበኝ አካል ይቅርታ ከጠየቁኝ ችግር የለውም፤ ይቅርታ የማይጠይቁኝ ከሆነ ግን ጉዳዩ በወንጀል ይታይልኝ ማለታቸውን ፖሊስ የማረጋገጫ ደብዳቤ ለችሎቱ መላኩ ተገልጿል።

ይሁንና እስክንድር በበኩላቸው ያስደበደበኝ አካል ይቅርታ የማይጠይቀኝ ከሆነ አሁንም ፖሊስ ምርመራውን እንዲጨርስ ይታዘዝልኝ ሲሉ ችሎቱን ጠይቀዋል።

ፍርድ ቤቱም ፖሊስ በእስክንድር ላይ የደረሰውን ጉዳት አጣርቶ በቀጣይ ቀጠሮ እንዲያቀርብ አዟል።

ፍርድ ቤቱ መዝገቡን መርምሮ ብይን ለመስጠት ለጥር 15፣ 2014 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

Add a review

The comment language code.

Restricted HTML

  • Allowed HTML tags: <a href hreflang> <em> <strong> <cite> <blockquote cite> <code> <ul type> <ol start type> <li> <dl> <dt> <dd> <h2 id> <h3 id> <h4 id> <h5 id> <h6 id>
  • Lines and paragraphs break automatically.
  • Web page addresses and email addresses turn into links automatically.