ፍርድ ቤቱ በእነ እስክንድ ነጋ መዝገብ ‘ክርክር ለማድመጥ ዳኞች አልተሟሉም’ ሲል ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጠ

መጋቢት 28፣ 2013 - ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የካቲት 30፣ 2013 በዋለው ችሎት ተከሳሾች ባለመቅረባቸው ምክንያት  ምስክር የማሰማት ሒደቱ ከማጋረጃ ጀርባ መሆን አለበት የለበትም የሚለውን ለመወሰን ሁለቱንም ወገኖች ቀርበው ክርክር እንዲያደርጉ ትዕዛዝ በመስጠት በክርክራቸው መሠረት  ብይን ለመስጠት  ለመጋቢት 28 ቀጠሮ ሰጥቶ እን እንደነበር የሚታወስ ነው።

ይሁንና በዛሬው ችሎት ዳኞች  ስላልተሟሉ ክርክር መስማት እንደማይችሉ አሳውቀዋል።

ይግባኝ ጠያቂው ዐቃቤ ሕግ  ባለፈው ችሎት ቀርበው የቀጠሮ ቀን የወሰዱ ቢሆንም እንኳን  የዛሬው ችሎት ‘ቀጠሮ አልደረሰንም፤ ክርክር ማድረግ አንችልም’ ሲሉ ተደምጠዋል።

ተከላካይ ጠበቆች በበኩላቸው የዐቃቤ ሕግ ድርጊት ሆን ተብሎ የተደረገ ስለሆነ ችሎቱ ትዝብት እንዲወስድላቸው እና ተከሳሾችን መንግሥት ለምርጫ ስጋቴ ነው ብሎ የሚያስባቸው ስለሆኑ ከምርጫ ለማስወጣት የተደረገ ክስ ስለሆነ ችሎቱ ይሄን ታሳቢ በማድረግ አጭር ቀጠሮ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል። በዚሁ ተለዋጭ ቀነ ቀጠሮ ለሚያዝያ 15፣ 2013 ተሰጥቷል።

Add a review

The comment language code.

Restricted HTML

  • Allowed HTML tags: <a href hreflang> <em> <strong> <cite> <blockquote cite> <code> <ul type> <ol start type> <li> <dl> <dt> <dd> <h2 id> <h3 id> <h4 id> <h5 id> <h6 id>
  • Lines and paragraphs break automatically.
  • Web page addresses and email addresses turn into links automatically.