ፍርድ ቤቱ ዐቃቤ ሕግ በእነ ጃዋር መሐመድ መዝገብ ምስክሮች በዝግ ችሎት እንዲሰሙ ያቀረበውን ጥያቄ ውድቅ አደረገ

መጋቢት 28፣ 2013 - በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አንደኛ የፀረ ሽብር እና ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች ችሎት ጃዋር መሐመድን ጨምሮ ሁሉም ተከሳሾች ቀርበዋል። ዐቃቤ ሕግ ባለፈው ችሎት በምስክር ጥበቃ አዋጅ መሠረት ለምስክሮቼ ደኅንነት ሲባል ከማጋረጃ በስተጀርባ እና በዝግ ችሎት ምስክሮቼን ላሰማ ሲል አቤቱታ ማቅረቀቡ የሚታወስ ነው።

ተከሳሾችም ዐቃቤ ሕግ ባቀረቡት ጥያቄ ላይ የመከላከል መብታችንን የሚገድብ ስለሆነ፣ እንዲሁም የዐቃቤ ሕግ ምስክሮች ተዓማኒነት ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ ስለሆነ ጥያቄው ውድቅ እንዲደረግላቸው ጠይቀዋል። በተጨማሪም የምስክር ዝርዝር ይገለጽልን ብለው አቤቱታ አቅርበዋል።

ፍርድ ቤቱ የሁለቱንም ወገን አቤቱታዎች ተመልክቶ ዐቃቤ ሕግ ባለፈው ችሎት በምስክር ጥበቃ አዋጅ 699/2009 አንቀጽ4/1 ሸ እና ቀ መሰረት ለ146 ምስክሮች ጥበቃ ተደርጓል ከማለት የዘለለ ምስክሮች ላይ ሊደርስ የሚችለውን ጉዳት በማስረጃ ያላሳየ በመሆኑ እና በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 20 መሠረት ተከሳሾች ለሕዝብ ግልጽ በሆነ ችሎት የመደመጥ መብት እንዳላቸው በመግለጽ ችሎቱ የምስክሮቹ ዝርዝር ሳይገለጽ በግልጽ ችሎት ምስክርነታቸውን እንዲሰጡ ብይን ሰጥቷል። ባለፈው ችሎት በተከላካይ ጠበቆች ቀርቦ የነበረውን የዋስትና ጥያቄ ችሎቱ ውድቅ በማድረግ የዐቃቤ ሕግ ምስክር ለመስማት ለሚያዝያ 5 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

Add a review

The comment language code.

Restricted HTML

  • Allowed HTML tags: <a href hreflang> <em> <strong> <cite> <blockquote cite> <code> <ul type> <ol start type> <li> <dl> <dt> <dd> <h2 id> <h3 id> <h4 id> <h5 id> <h6 id>
  • Lines and paragraphs break automatically.
  • Web page addresses and email addresses turn into links automatically.