በእነ ስብሓት ነጋ መዝገብ ዐቃቤ ሕግ የቅድመ ምርመራ ምስክር ለመሰማት በተያዘለት ቀጠሮ ሳይደመጥ ታገደ

መጋቢት 29፣ 2013 - እነ ስብሓት ነጋ በዐቃቤ ሕግ የቅድመ ምርመራ ምስክር አሰማም ሒደትን በተመለከተ ለከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ማለታቸው የሚታወስ ነው። ችሎቱ የቅድመ ምርመራ ምስክር ለመስማት ተሰይሞ የነበረ ቢሆንም፥ የምስክር አሰማሙ ላይ በከፍተኛ ፍርድ ቤት የይግባኝ እግድ በመጣሉ እግዱ እስከሚነሳ ድረስ መዝገቡን መዘጋቱን አሳውቋል።

ይህን ተከትሎ ዐቃቤ ሕግ ይግባኝ ለተባለበት ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዛሬውኑ ክርክር እናድርግበት ብሎ ቢያመለክትም፣ ችሎቱ የሥራ ጫና ስላለብኝ እንዲሁም ከይግባኝ ሰሚ ችሎቱ አንዱ ዳኛ በሕመም ምክንያት ስላልተገኙ ማከራከር አልችልም ብሏል። በይግባኙ ላይ ክርክር ለማድረግ ለሚያዝያ 6፣ 2013 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥተዋል።

Add a review

The comment language code.

Restricted HTML

  • Allowed HTML tags: <a href hreflang> <em> <strong> <cite> <blockquote cite> <code> <ul type> <ol start type> <li> <dl> <dt> <dd> <h2 id> <h3 id> <h4 id> <h5 id> <h6 id>
  • Lines and paragraphs break automatically.
  • Web page addresses and email addresses turn into links automatically.