በእነ እስክንድር ነጋ መዝገብ ዐቃቤ ሕግ ሁለተኛ የምስክሮች ማድመጫ ቀጠሮውን ሳይጠቀምበት ቀረ

ሐምሌ 9፣ 2013፤ በዛሬው ችሎት እነ እስክንድር ነጋ ከትላንቱ በተመሳሳይ መልኩ ብዙ ደጋፊዎቻቸው በተገኙበት ተደጧል። ችሎት ከመጀመሩ በፊት ፍርድ ቤቱ ታዳሚዎችን በሚመለከት የችሎቱን ሐደት ቀርፃችሁ በማኅበራዊ ድረገጾች ላይ መልቀቃችሁን ስለተመለከትን ከዚህ ድርጊት እንድትቆጠቡ ሲሉ ትዕዛዝ ሰጥቷል።

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ የፀረ ሽብረ እና የሕገ መንግሥት ጉዳዮች ወንጀል ችሎት፣ ጉዳዩን ያሳደረው የዐቃቤ ሕግ ምስክሮችን ለማድመጥ ቢሆንም፣ እንኳን የዐቃቤ ሕግ ግን ምስክሮች ለማድመጥ በተቀመጡት የመጨረሻ ቀናቶች ላይ ማለትም በሐምሌ 15 እና 16 ላይ ማቅረብ መብት ስላለኝ እስከዛን ቀን ዝግጅቴን ጨርሼ ምስክሮቼን አሰማለሁ ብሏል።

ተከላካይ ጠበቆች በበኩላቸው በቀጠሮ ቀን ምስክር ያለማቅረብ መብት አለመሆኑን እና ፍርድ ቤቱ በአፅንዖት እንዲያይላቸው የጠየቁ ሲሆን፣ ዐቃቤ ሕግ በሚፈልጉት ቀን ማሰማት መቻል የችሎቱን ትዕዛዝ እንዳለማክበር እና ሥነ ስርዓታዊ እንዳልሆነ ገልጸዋል።

‘በተጨማሪም በቀን 5 ምስክር ለመስማት ነበር የቀጠሮ ቀናት የተሰጡጥ እንደ ዐቃቤ ሕግ ከሆነ ግን፣ በሁለት ቀን ሀያምናም ምስክር ሊያሰማ ነው። በዐቃቤ ህግ ቸልተኝነት የደንበኞቻችን መሠረታዊ መብቶች ላይ ሆን ተብሎ ጉዳት እንዲደርስባቸው እየተደረገ ነው። መዝገቡ ተቋርጦ ይሸኙን’ ብለዋል።

ፍርድ ቤቱ ትላንት ትዕዛዝ ሳይሰጥበት ያለፈውን በስንታየሁ ቸኮል ላይ ትዕዛዝ ሰጥቶበታል። የወንጀለኛ መቅጫ ሕጉን መሰረት ያደረገ እና የችሎቱን ክብር በጠበቀ መልኩ ንግግር እንዲያደርጉ ሲል አዟል። በተጨማሪም ችሎቱ “ዐቃቤ ሕግ ረዥም ቀጠሮ መጠየቅ አይችልም እንጂ፣ እኛ ባስቀመጥነው የቀጠሮ ቀናቶች ማቅረብ ይችላል” በማለት ቀጣይ ቀጠሮ ለ ሐምሌ 14, 15 እና 16 ምስክር እንዲያቀርብ ትዕዛዝ ሰጥተዋል።

በትናንትናው ቀጠሮ ዐቃቤ ሕግ ምስክሮቼን ደኅንነታቸውን ለመጠበቅ አድራሻቸውን መቀየር ስላለብኝ ተጨማሪ ጊዜ ይሰጠኝ የሚል አቤቱታ አቅርቦ በችሎቱ ተቀባይነት ማጣቱን ዘግበን ነበር።

Add a review

The comment language code.

Restricted HTML

  • Allowed HTML tags: <a href hreflang> <em> <strong> <cite> <blockquote cite> <code> <ul type> <ol start type> <li> <dl> <dt> <dd> <h2 id> <h3 id> <h4 id> <h5 id> <h6 id>
  • Lines and paragraphs break automatically.
  • Web page addresses and email addresses turn into links automatically.