በእነ እስክንድር ነጋ መዝገብ የዐቃቤ ሕግን ምስክር ለማድመጥ የተያዘው ቀጠሮ አዲስ ዳኞች በመተካታቸው ምክንያት ተለዋጭ ቀጠሮ በድጋሚ ተሰጠበት

ጥቅምት 04፣ 2014 – ፍርድ ቤቱ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አንደኛ የፀረ ሽብር እና ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች ችሎት በእነ እስክንድር ነጋ መዝገብ የዐቃቤ በሕግ ምስክር ለማሰማት በዛሬው ዕለት ቀጥሮ እንደነበር ይታወሳል።

ከዚህ ቀደም በነበረው ችሎት የዐቃቤ ሕግ ምስክር በቀን አራት እንዲቀርብ ችሎቱ ትዕዛዝ ሰጥቶ የነበረ ቢሆንም፤ ዐቃቤ ሕግ ግን ሁለት ምስክሮች በቀን እንደሚያስደምጥ ለችሎቱ አሳውቋል።

ይህን ተከትሎ  በተከላካይ ጠበቆች በኩል ተቃውሞ ቀርቦበታል። ከዚ በፊት በችሎቱ በተሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በጥቅምት 4፣ 5፣ 8፣ 9 እና 10 በቀን አራት ምስክር መደመጥ እንዳለበት ትዕዛዝ መሰጠቱ የሚታወቅ መሆኑን በማስታወስ፤ ዐቃቤ ሕግ በዚህ ትዕዛዝ መሠረት ያቅርብልን ያሉ ሲሆን፥ በተጨማሪም ምስክር በሚሰማበት ቀን ምስክሮች የሥም ዝርዝር ሊሰጠን ይገባል በማለት ተከራክረዋል።  

ዐቃቤ ሕግ በበኩሉ ከግዜ አንጻር በቀን ሁለት ብቻ ለማቅረብ ያሰበነው እንጂ የተቀሩትንም ማቅረብ ይቻላል፤ ነገር ግን ካለን ግዜ አንጻር የተቀሩት ምስክሮች ማቅረቡ  ምስክርነታቸውን  ሳይሰጡ እንግልት ብቻ እንዳይሆንባቸው በማሰብ ነው ብሏል።

ከዚህ ቀደም ይህን መዝገብ ሲያዩ የነበሩት ሦስቱም ዳኞች ዛሬ ባሉት አዲስ ዳኞች በመተካታቸው፣ ዛሬ የተሰየሙት ዳኞች  ለጉዳዩ አዲስ በመሆናቸው መዝገቡን በአግባቡ ሳያዩ ምስክር መስማት ከባድ ስለሚሆንብን፣ በማለት ዐቃቤ ሕግ በነገው ዕለት የምስክሮችን የሥም ዝርዝር እና ምስክሮችን ይዞ እንዲቀርብ ትዕዛዝ ሰጥቷል።

በመዝገቡ ሁለተኛ ተከሳሽ የሆኑት ስንታየሁ ቸኮል በማረሚያ ቤት እየተሰጠኝ ያለው ሕክምና በቂ ስላልሆነ (ሕምሜ ከማረሚያ ቤቱ አቅም በላይ ስልሆነ) በግል መታከም እንድችል ፍርድ ቤቱ ትዕዛዘ እንዲሰጥልኝ ሲሉ አቤቱታ አቅርበዋል። አራተኛ ተከሳሽ የሆኑት አስካል ደምሌ በቁጥጥር ስር በዋሉበት ግዜ ተወርሶ የነበረው  የእጅ ስልካቸው ሰሞኑን በማረሚያ ቤት በኩል እንዲመለስላቸው መደረጉን እና ነገር ግን በስልኩ ላይ የነበሩት ማስረጃዎቻቸው በሙሉ የጠፉ በመሆኑ እንዲመለስለኝ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ይስጥልኝ ሲሉ ጠይቀዋል።

Center for Advancement of Rights and Democracy (CARD)

Making Democracy the Only Rule of Game!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *