እነ ብርጋዴር ጄኔራል ምሩፅ ከውጭ ሁነው እንዲከታተሉ የተወሰነው በከፍተኛ ፍርድ ቤት ተሻረ፤ ኮሎኔል ተስፋዬ ሓጎስ ፍ/ቤት አልቀረቡም

ቀን፡ ታኅሣሥ 01/2013 - ሰዓት፡ ከረፋዱ 4፡45 - በፌደራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ አንደኛ ወንጀል ችሎት ሐሙስ ታኅሣሥ 01 ቀን 2013 በዋለው ችሎት ፍርድ ቤቱ ለመርማሪ ፖሊስ በእነ ብርጋዴር ጄኔራል ምሩፅ በርሄና ሌሎች ተጠርጣሪዎች ተጨማሪ ቀነ ቀጠሮ ሰጥተዋል። በዚህ መዝገብ ከተካተቱት ተጠርጣሪዎች በችሎቱ ከኮሎኔል ተስፋዬ ሓጎስ በስጠቀር ሌሎቹ ቀርበዋል። ኮሎኔል ተስፋዬ ሓጎስ በባለፈው ችሎት ፍርድ ቤቱ በዋስ ተለቀው ጉዳያቸውን ከውጭ ሁነው እንዲከታተሉ ቢፈቅድላቸውም፣ ውሳኔው በከፍተኛ ፍርድ ቤት እንደተሻረ ተገልጿል። ነገር ግን መርማሪ ፖሊስ ይህንን የሚያስረዳ የጽሑፍ ማስረጃ አላቀረቡም። በተጨማሪም ኮሎኔል  ተስፋዬ ሓጎስ ያልቀረቡበት ሁኔታ አልታወቀም።

በዋለው ችሎት ላይ መርማሪ ፖሊስ ተጠርጣሪዎች ሕወሓት አመራሮች ጋር ኔትወርክ በመፍጠር ሠራዊቱ ላይ ጥቃት እንዲደርስ አሲረዋል፣ ሥልጣን ያላግባብ ተጠቀመዋል፣ የጥፋት ተልዕኮ ሰጥተዋል፣ የተሳሳተ መረጃ ለመከላከያ ሠራዊቱ አቀብለዋል በሚሉ እና በሌሎችም ተጓዳኝ ጥፋቶች እንደተሳተፉ የሚያመላክቱ የሰው፣ የሰነድና የኤሌክትሮኒክ መረጃዎች እንዳሉ ገልጧል። በተጨማሪም መርማሪ ፖሊስ የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ፣ ፍላሽና የላፕቶፖች መረጃዎች ለብሔራዊ መረጃ ደኅንነት እንዲጣራ ስለሰጠ እና የተመደቡ መርማሪ ፖሊሶች ባለው የአገሪትዋ ሁኔታ ሥራቸውን በተቀላጠፈ ሁኔታ መወጣት ስላልቻሉ እንዲሁም የወንጀሉን ውስብስብነት  በመመልከት ፍርድ ቤቱ ተጨማሪ 14 የምርመራ ቀናት እንዲፈቅድ በመርማሪ ፖሊስ ጠይቀዋል። በሌላ በኩል ተከሳሾቹ በሥራም ሆነ በግል ሕይወት ካሁን በፊት እንደማይተዋወቁ፥ እንዲሁም 1ኛ ተጠርጣሪ ብርጋዴር ጄነራል ምሩፅ በርሄ የተጠረጠሩበት ወንጀል በጭራሽ እንደማይመለከታቸዉ፤ 2ኛ ተጠርጠሪ ኮሎኔል ገብረመድኅን ገብረመስቀል ወንጀሉን ተፈፀመ በተባለበት ወቅት በሥራ ምክንያት ከአገር ውጪና ለረጅም ግዜ ደሞ በኮረና ሕመም ምክንያት ማቆያ ውስጥ (ኳራንቲን) አንደነበሩ፣ 4ኛ ተጠርጣሪ ኮሎኔል መብራቱ ታደሰ ጡረተኛ እንደሆኑ ወንጀሉን ለመፈፀም አቅሙ እደሌላቸው እና እደማይችሉ፣ በተጨማሪም የክሱን አመሠራረት እና አደረጃጀት በመቃወሞ የመከላከያ ሞክንያቶች በሰፊው አቅርበዋል። ተጠርጣሪዎቹ መርማሪ ፖሊስ የሚያስፈልገውን መረጃ ወስዷል፤ ምስክሮችም አሉኝ ስላለ ተጨማሪ የግዜ ቀጠሮ ሊሰጥ አይገባም በሚል የዋስትና መብታቸው እንዲከበርላቸው ተከራክረዋል። በመጨረሳም ፍርድ ብቱ የሁለቱን ወገኖች ክርክር ካዳመጠ በኋላ ለታኅሣሥ 13 ቀን 2013 ተጨማሪ 12 ቀናት ቀነ ቀጠሮ ሰጥቷል።

Add a review

The comment language code.

Restricted HTML

  • Allowed HTML tags: <a href hreflang> <em> <strong> <cite> <blockquote cite> <code> <ul type> <ol start type> <li> <dl> <dt> <dd> <h2 id> <h3 id> <h4 id> <h5 id> <h6 id>
  • Lines and paragraphs break automatically.
  • Web page addresses and email addresses turn into links automatically.