እነ ጃዋር መሐመድ በፍትሕ ስርዓቱ ላይ እምነት ስላጣን ፍርድ ቤት አንቀርብም አሉ

ሰኔ 21፣ 2013፤ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ የፀረ ሽብረ እና የሕገ መንግሥት ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ቀጠሮ የያዘው ዐቃቤ ሕግ አሻሽሎ ባቀረበው አቤቱታ ላይ ክርክር እንዲደረግበት ቢሆንም እንኳን ጃዋር መሐመድ፣ በቀለ ገርባ፣ ሃምዛ አዳነ፣ ደጀኔ ጣፎ፣ አረፋት፣ ሸምሰዲን ጠሃ፣ ሻለቃ ኬኔ፣ እና ሃ/አለቃ ዳንኤል ባለመቅረባቸው ምክንያት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

በችሎቱ ጥያቄ መሠረት የማረሚያ ቤት ጉዳይ አሰፈፃሚ ተከሳሾች በገዛ ፍቃዳቸው ችሎት አንቀርብም በማለታቸው ማረሚያ ቤቱ ማቅረብ እንዳልቻለ አስረድተዋል።

ተከላካይ ጠበቆች በበኩላቸው ከአንድ አስከ አራት ያሉ ተከሳሾች ወደ ችሎት ያልቀረቡበትን ምክንያት በጽሑፍ ልከዋል፣ 12ኛና እና 22ኛ ተከሳሾችን በሚመለከት የሆስፒታል ቀጠሮ ስላላቸው መቅረብ እንዳልቻሉ ምላሽ ሰጥተውበታል።

ፍርድ ቤቱም በተከሳሾች በኩል የተላከውን ጽሑፍ ለችሎቱ በአጭሩ አንብበዋል "ፍርድ ቤቶች የሚሰጠው ውሳኔ በአስፈፃሚው አካል እየተከበረ ስላልሆነ እና የፍርድ ቤቱንም ሆነ የፖሊስ ግዜ ላለማባከን እንዲሁም የፍትሕ ስርዐቱ  ላይ እምነት መጣል ስላልቻልን በገዛ ፍቃዳችን ቀርተናል" ብለዋል።

 

እነ ጃዋር መሐመድ ለፍርድ ቤት የጻፉት ደብዳቤ

 

ዐቃቤ ሕግ ለችሎቱ ሁለት ሐሳቦችን አቅርቧል። ተከሳሾች የፍርድ ቤቱን ትዕዛዝ ስለሆነ የጣሱት በኃይል ማረሚያ ቤቱ እንዲያቀርባቸው ትዕዛዝ እዲሰጥላቸው እና በዚህ መሠረት መቅረብ የማይችሉ ከሆነ በጠበቃ የመወከል መብታቸው ተገፎ በሌሉበት ሒደቱ እንዲቀጥል ሲሉ ችሎቱን ጠይቀዋል።

ተከላካይ ጠበቆችም ተከሳሾች በሌላ ችሎት ያሉ ጓደኛቻቸው ላይ ነጻ ተብለው ግን ደብዛቸው ስለጠፋ (ያሉበት ስለማይታወቅ) በተፈጠረው ነገር ድንጋጤ እየተሰማቸው ስለሆነ ኃይል ሳያስፈልግ አጭር ቀጠሮ  ይሰጠንና አናግረናቸው ይቀርባሉ ያሉ ሲሆን፥ በተጨማሪም እስር ቤት ውስጥ ባሉ ተከሳሾች ጉዳያቸው በሌሉበት ይታይልኝ ያለው ዐቃቤ ህግ  የሥነ ስርዓት ሕጉን ስለሚቃረን ችሎቱ ውድቅ እንዲያደርግላቸው ጠይቀዋል።

ችሎቱም ተከሳሾች ያቀረቡት ምክንያት እና የቀሩበት ጉዳይ አጠያያቂ ነው በማለት "እኛ ላይ ጫና በመፍጠር የሚመጣ ለውጥ የለም፤ ችሎቱንም እራሳቸውንም ነው የሚጎዱት" የሚል አስተያየት በመስጠት ሦስት ትዕዛዝ አስተላለፏል። ጠበቆች በሬጂስትራር በኩል ለሰኔ 28 በዐቃቤ ሕግ አቤቱታ ላይ ምላሽ እንዲያስገቡ፣ 1ኛ፣ 2ኛ፣ 3ኛ፣ እና 5ኛ ተከሳሾች በየሥማቸው መጥሪያ ተሰጥቷቸው እንዲቀርቡ፣ 7ኛ፣ 12ኛ፣ 13ኛ፣ 22ኛ እና 23ኛ (አረፋት፣ ወንደሰን፣ ሸምሰዲን፣ ሻለቃ ኬኔ፣ ሃ/አለቃ ዳንኤል፣ በቀለ) ተከሳሾች በሚመለከት የቀሩበትም ምክንያት ከመግለጫ ጋር እንዲያቀርቡ ቀጣይ ቀጠሮ ለሰኔ 29 ሰጥተዋል።

Add a review

The comment language code.

Restricted HTML

  • Allowed HTML tags: <a href hreflang> <em> <strong> <cite> <blockquote cite> <code> <ul type> <ol start type> <li> <dl> <dt> <dd> <h2 id> <h3 id> <h4 id> <h5 id> <h6 id>
  • Lines and paragraphs break automatically.
  • Web page addresses and email addresses turn into links automatically.