ካርድ በሐሳብን የመግለጽ ነጻነት፣ የጥላቻ ንግግር እና ምርጫ ጉዳይ የውይይት መድረክ አሰናዳ
ካርድ ከአምሃ መኮንን እና አጋሮቹ የሕግ ቢሮ እና የኢትዮጵያ ዲጂታል መብቶች ቡድን ጋር በመተባበር የውይይት መድረክ አሰናዳ። የውይይት መድረኩ “ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት፣ የጥላቻ ንግግር እና ምርጫ በኢትዮጵያ” በሚል ርዕስ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት እና ብዙኀን መገናኛዎች በተገኙበት የካቲት 21 ፣ 2012 በኢንተር ኮንቲነንታል አዲስ ሆቴል ለግማሽ ቀናት ተካሒዷል። የውይይት መድረኩ ያስፈለገው ዜጎች ሐሳባቸውን በነጻነት በሚገልጹበት ጊዜ የጥላቻ ንግግርን እና የሐሰት መረጃን ከማሰራጨት እንዲቆጠቡ እንዲሁም መንግሥት የጥላቻ ንግግሮችን በሕግ አግባብ ለመቆጣጠር ሲሞክር ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት አደጋ ላይ እንዳይወድቅ ለማድረግ የሚያስችሉ ሐሳቦች ላይ ለመምከር ነው።
በውይይት መድረኩ ላይ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሰብኣዊ መብቶች ማዕከል ዳይሬክተር ወንድማገኝ ታደሰ ጥናታዊ ጽሑፍ ያቀረቡ ሲሆን፣ አምሃ መኮንንም በቅርቡ በፀደቀው የፀረ ጥላቻ ንግግር አዋጅ ይዘት ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል። የውይይት መድረኩ ከተሳታፊዎች ለቀረቡ አስተያየቶች እና ጥያቄዎች አምሃ መኮንን እና ወንድማገኝ ታደሰ መልስ እንዲሰጡ አስችሏል።
ጥናቱ እና የውይይት መድረኩን ድጋፍ እንዲካሔድ ድጋፍ ያደረገው ናሽናል ኢንዶውመንት ፎር ዲሞክራሲ ነው።
Add a review