ዐቃቤ ሕግ በእነ እስክንድር ነጋ ላይ የሚቀርቡ የምስክሮችን የሥም ዝርዝር በሚዲያ እንዳይቀርብ አቤቱታ አቀረበ

ጥቅምት 05፣ 2014 - ፍርድ ቤቱ በጠዋቱ በተሟላ ችሎት ዐቃቤ ሕግ የምስክር ዝርዝር እና የምስክር ጭብጥ በግልጽ አለማቅረቡን ተከትሎ ማን በማን በየትኛው የሚለው ተለይቶ ከሰዓት ላይ እንዲያቀርብ ታዞ ነበር።

ይሁንና ፍርድ ቤቱ ከሰዓት ከያዘው የቀጠሮ ሰዓት በማሳለፍ ባልተሟላ ዳኛ በተሰየመበት በዚህ መዝገብ ዐቃቤ ሕግ በእነ እስክንድር ነጋ ላይ የሚቀርቡ 9 ምስክሮችን ዝርዝር በሚዲያ እንዳይቀርብ አቤቱታ በጽሑፍ አስገብቷል። በተያያዘም ከ9 ውጪ ያሉ ምስክሮቼ መመስከር እንደሚፈልጉ ፍቃዳቸውን ጠይቀን ከተስማሙ የምናመጣቸው ይሆናል ሲል ማብራሪያ ሰጥቷል።

ተከላካይ ጠበቆች በበኩላቸው ዐቃቤ ሕግ 15 ወር ሙሉ የተለያዩ ምክንያቶች በመጠቀም መዝገቡ በፈጣን ሁኔታ እልባት እንዳያገኝ አንጓትቶብናል ያሉ ሲሆን፥ ጠዋት በተሟላ ዳኛ የምስክር ጭብጥ እና ዝርዝር ዐቃቤ ሕግ እንዲያቀርብ የታዘዘውን እየጣሰ በመሆኑ በጠዋቱ ትዕዛዝ መሠረት ስርዓቱን እንዲያስፈጽም ሲሉ ጠይቀዋል።

ዐቃቤ ሕግ በበኩሉ ‘እኛ ዳኝነት ነው የጠየቅነው፤ እንደኛ ፍላጎት ቢሆን የምስክር ሥም ዝርዝር አስቀድመን ባላቀረብን ነበር። ነገር ግን በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታዎች ሊከሰት የሚችል አደጋን ለመቀነስ ነው አየሰራን ያለነው’ ሲል ምላሽ ሰቷል።

አንደኛ ተከሳሽ እስክንድር ነጋ በበኩላቸው ምስክሮች እንዲፈሩ ሳይሆን እውነታውን ሕዝብ እንዲረዳን ሥም ዝርዝራቸው በሚዲያ እንዲቀርብ እንፈልጋለን ሲሉ ትዕዛዝ እንዲሰጥላቸው ችሎቱን ጠይቀዋል።

የችሎቱ የቀኝ ዳኛ በቤተሰብ በሕመም ምክንያት አለመኖራቸውን ተከትሎ ሌሎች ዳኞች ለማሟላት ተሞክሮ ሥልጠና ሔደዋል በመባሉ ምክንያት፣ ችሎቱ ተሟልቶ አለመቅረቡ በመሐል ዳኛው ተብራርቷል። ይሁንና ችሎቱ ባልተሟላበት ሁኔታ  በቀረበው አቤቱታና ክርክር ላይ ትዕዛዝ መስጠት እንደማያስችል ተገልጿል።

ሁለተኛው ተከሳሽ ስንታየሁ ቸኮል በግሌ ልታከም በማለት ያቀረቡትን አቤቱታ በተመለከተ በቀጣዩ ቀጠሮ ማረሚያ ቤት አስተያየት እንዲሰጥበት ታዟል።

ዐቃቤ ሕግ ማረሚያ ቤቱ በሥራችን ስለሆነ አስተያየት  እንስጥበት ያለ ሲሆን፥ ከማረሚያ ቤት አስተያየት በኋላ አስተያየት እንደሚሰጡበት ተጠቁሟል።

በተነሱ ክርክሮች ላይ በተሟላ ችሎት ትዕዛዝ ለመስጠት ለፊታችን ማክሰኞ ቀጠሮ ተይዟል።

Add a review

The comment language code.

Restricted HTML

  • Allowed HTML tags: <a href hreflang> <em> <strong> <cite> <blockquote cite> <code> <ul type> <ol start type> <li> <dl> <dt> <dd> <h2 id> <h3 id> <h4 id> <h5 id> <h6 id>
  • Lines and paragraphs break automatically.
  • Web page addresses and email addresses turn into links automatically.