የታህሳስ 08-2013 አቶ ጃዋር መሀመድ እና በቀለ ገርባ የችሎት ውሎ – ፍርድ ቤቱ እነ አቶ ጃዋር ተገደው ችሎት እንዲቀርቡ ውሳኔ አሳልፏል፤ ለጥር04 ተለዋጭ ቀጠሮ ተይዟል

ቀን ታህሳስ 8/2013

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የልደታ ምድብ ችሎት በታህሳስ 08/2013 በዋለው ችሎት የእነጃዋር  መሀመድ የክስ መዝገብን ተመልክቶ ውሳኔ ሰጥተዋል። በውሳኔው መሰረት ከዚህ በፊት በእነ ጃዋር መሀመድ መዝገብ ስር የተከሰሱት አራት ተከሳሾች ማለትም አቶ ጀዋር መሀመድ፣ በቀለ ገርባ፣ ሀምዛ አዳነ (ሀምዛ ቦረና) እና ሸምሰዲን ጠሀ ለደህንነታችን ስለምንሰጋ በአቅራቢያችን ማለትም ቃሊቲ ማረሚያ ቤት አቅራቢያ ችሎት እንሲሰየምለን ብለው ያቀረቡት አቤቱታ በፍርድ ቤቱ ውድቅ ተደርጓል። በመዝገቡ ስር ከተከሰሱት ውስጥ አቤቱታ አቅራቢዎቹ በችሎት ያልቀረቡ ሲሆን የተቀሩት ተከሳሾች ችሎቱ ላይ ተገኝተዋል።

ችሎቱ እንደገለጸው አንድን ችሎት የማደራጀው በእቅድ፣ በጥናት እና በህግ መሰረት መሆኑን ፤ እንዲሁም በአቤቱታ እና በዘፈቀደ በተገልጋይ ፍላጎት ብቻ እንደማይቀየር ነገር ግን ፍርድ ቤቱ ካመነበት እንደሚቻል አስረድተውል። በመሆኑም በአራቱ ተከሳሾች የቀረበው አቤቱታ በማስረጃ ያልተደገፈ በመሆኑ አቤቱታውን ውድቅ በማድረግ ጉዳዩ በዚሁ ችሎት (በልደታ ምድብ ችሎት) እንዲታይ ፍርድ ቤቱ  በመወሰን ለጥር 25 ቀን 2013 ተለዋጭ ቀጠሮ የወሰነ ቢሆንም ። የተከሳሽ ጠበቆች በቃረቡት አቤቱታ የቀጠሮው ቀን እንዲቀየር ተደረጓል።

በጠበቆች ከተነሱ ነጥቦች ውስጥ አቤቱታ ያቀረቡ ተከሳሾች ግዚያዊ ችሎት በአቅራቢያችው እንዲደራጅ የጠየቁት “በሀገራችን ባለን ጉልህ ሚና፣ በሀገሪትዋ ባለው የፖለቲካ ትኩሳት፣ በተነዛብን የሚድያ ፕሮፖጋንዳና እንዲሁም የችሎቱ ቦታ ካለንበት ማረሚያ ቤት ርቀት ስላለው ለአደጋ ተጋላጭ በመሆናችን እና ስጋት ስላለብን” ስለሆነ አቤቱታው በድጋሚ እንዲታይ እና የተሰጠው ቀነ ቀጠሮ የተራዘመ ስለሆነ ፍርድ ቤቱ እንዲያሳጥረው በአጽኖት ጠይቅዋል። በተጨማሪም ጉዳዩ ሀገራዊና ዐለም አቀፍ ትኩረት ስላለው፣ ተከሳሾች ለመጣው ለውጥ ግምባር ቀደም ተዋናዮች እና የአንበሳውን ድርሻ የነበራቸው ስለሆነ እንዲሁም የችሎቱ መራዘም በመጪው ምርጫ ተጽኖ ስለሚኖረው የችሎቱ ቀጥሮ እንዲያጥር በጠበቆች ጥያቄ ቀርቧል። እንዲሁም ካሁን በፊት 6ኛ፣ 16ኛ እና 17ኛ ተከሳሾች ቤተሰቦቻቸው በውጭ ሀገር ስለሚኖሩ በስልክ እንዲገናኙ የቀረበ አቤቱታ ቢኖርም ምላሽ አልተሰጠውም፤ ሌሎቹ ተከሳሾችም ከቤተሰቦቻቸው ጋር በስልክ ግንኙነት እንዲያደርጉ ጠበቆች ጠይቀዋል። ከተከሳሾች መሀል አቶ ደጄኔ ጣፋ እንዲናገሩ በመጠየቃቸው ተፈቅዶላቸው ሀሳባቸውን እነደሚከተለው አቅርበዋል፤ “የተሰጠው ቀነ ቀጠሮ በጣም የተራዘመ ነው፤ ብይን ለመስጠት ካሁን በፊት ይሄን ያህል ግዜ ተቀጥሮ አያውቅም። ቢበዛ ከ15 እስከ 20 ቀን ይበቃል፤ ስለሆነም ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን ባፋጣኝ መርምሮ መልስ ይስጥን ... የተከሰስነው የፖለቲካ ሰዎች ስለሆንን ነው...” ብለዋል።

ዐቃቤ ህግ ጠበቆች በሚያቀርቡት መቃወምያ ክርክር መሀል ጣልቃ በመግባት ሊያስቆማቸው ቢሞክርም ዳኞች ጠበቆችን ሀሳባቸው እንዲጨርሱ በመፍቀድ፥ ከጨረሱ በሁላ በመቀጠል ዐቃቤ ህግ ሀሳቡን እንዲያቀርብ ተፈቅዶለታል። በዚህም መሰረት ዐቃቤ ህግ “ችሎቱ በሚመቸው ቀን ቀጠሮ ቢሰጥ መልካም ነው፤ ነገር ግን የችሎቱ ታዳሚዎች የተሳሳተ ግንዛቤ ይዘው መውጣት የለባቸውም፣ ተከሳሾች ችሎት አንቀርብም ካሉ ተገደውም ቢሆን መቅረብ ኣለባቸው፣ ይህ የፍርድ ቤት ችሎት  እንጂ የፖለቲካ ክርክር መድረክ አይደለም ስለዚህ ክርክሩ ከህግ ማእቅፍ ነው መሆን ያለበት...” በማለት ሃሳቡን አቅርቧል። ፍርድ ቤቱ ክርክሩን ካዳመጠ በሁላ “ተከሳሾች ችሎት እንዲቀርቡ ብዙ ጥረት እንዳደረገ፣ በተከሳሾች የቀረበ አቤቱታ በማስረጃ የተደገፈና በቂ ባለመሆኑ ውድቅ መደረጉን፣ ፍርድ ቤቱ የስራ ጫና ስላለበት ጉዳዩን ግዜ ወስዶ በደንብ ለማየት እንዲረዳው ረዘም ያለ ቀጠሮ መሰጠቱን እና እንዲሁም ለምርጫ ተብሎ የሚያጥር ወይም የሚራዘም የፍርድ ቤት ቀጠሮ እንደሌለ...” ሰፋ ያለ ማብራርያ በመስጠት የሚከተሉትን ውሳኔዎች አስተላልፈዋል። ለጥር  25 ቀን 2013 ዓ.ም ተሰጥቶ የነበረዉ ቀነ ቀጠሮ በማሻሻል ለጥር 4 ቀን 2013 ተደርጓል። በመቀጠልም ሁሉም ተከሳሾች በሀገር ውስጥም ከሀገር ውጭም ካሉ ቤተሰቦቻቸው ጋር በስልክ እንዲገናኙ ተፈቅደዋል። አንደኛ፣ ሁለተኛ፣ አስራሶስተኛ እና አስራአራተኛ ተከሳሾች በቀጣይ ችሎት እንዲቀርቡ፤ የማይቀርቡ ከሆነ የማረሚያ ቤቱ ፖሊስ አስፈላጊውን እርምጃ ተጠቅሞ ባስገዳጅ ሁኔታ እንዲያቀርባቸው ትእዛዝ ለማረሚያ ቤቱ አስተላልፈዋል።

Add a review

The comment language code.

Restricted HTML

  • Allowed HTML tags: <a href hreflang> <em> <strong> <cite> <blockquote cite> <code> <ul type> <ol start type> <li> <dl> <dt> <dd> <h2 id> <h3 id> <h4 id> <h5 id> <h6 id>
  • Lines and paragraphs break automatically.
  • Web page addresses and email addresses turn into links automatically.