ጋዜጠኛ ጌጥዬ ያለው ችሎት በመድፈር የሁለት ወር የእስራት ቅጣት ተጣለባቸው

ጥቅምት 23 2014 - የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ የፀረ ሽብርና  ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች ወንጀል ችሎት መዝገቡ የተቀጠረው ጌጥዬ ላይ ቅጣት ለማሳረፍ እና የዐቃቤ ሕግ ምስክር ለማሰማት ነው።

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት በእነ እስክንድር ነጋ የክስ መዝገብ የችሎት አዘጋገብ በተያያዘ ጌጥዬ ያለውን ችሎት በመድፈር ፍርድ ቤቱ ጥፋተኛ ብሎት የነበረ መሆኑ ይታወሳል።

ፍርድ ቤቱ ጥፋተኛ ነው ሲል በጠበቆች በኩል የተነሱ የቅጣት ማቅለያዎች በሙሉ ውድቅ አድርጓቸዋል። ችሎቱ ጌጥዬ ያለውን ያስተምራል ብሎ ያሰበውን የሁለት ወር እስራት እንዲቀጣ መወሰኑን ገልጿል።

የዐቃቤ ሕግ ስድስተኛ ምስክር ከባለፈው በቀጠለ ሐሳብ ላይ ቃላቸውን ሰተዋል፤ እስክንድር ነጋ ምስክሩን ለለቅሶ የሚመጡ ቄሮዎችን ደብድቡ ብለው የሰጧቸውን ትዕዛዝ፣  ምንም እንኳን ምስክሩ ኦሮሞ ቢሆኑም ትዕዛዙን የተቀበሏቸው በውስጥም በውጪም አሠራር በዓላማ ተመሳሳይ አቋም ስላላቸው እንደሆነ ለፍርድ ቤቱ ገልጸዋል ።

 በተጨማሪም የተሰጣቸውን ተልዕኮ በተዋረድ አደረጃጀት ተፈጻሚ እንደሚያደርጉ እና ግለሰቦቹ ትዕዛዝ ከሚሰጣቸው (ምስክሩ) አካል ውጪ ከላይ ባሉ የባልደራስ አመራሮችም ሆነ አባሎች እንደማይታወቁ አስረድተዋል፤ በዚህ መሠረትም በእሳቸው አደረጃጀት ሰኔ 23, 2012 በሥራቸው ተልዕኮ አስፈፃሚ (አልማው) ባስነሷቸው ረብሻ በአንፎ አካባቢ ሁለት ሰዎች መሞታቸውን እና ንብረት መውደሙ አልማው የሚባሉት ግለሰብ ደውለው እንደነገሯቸው፣ ነገር ግን ግድያው ቀጥታ በነሱ ይፈፀም አይፈፀም የሚያቁት ነገር እንደሌለ ጨምረው ገልጸዋል።

ምስክር ሰኔ 24, 2012 ላይ በነበረው ረብሻ እና ሁከት የማስነሳቱን ሒደት በስልክ ትዕዛዝ ከእስክንድር የሚቀበሉበትን ስልክ ቁጥር ለችሎቱ አስመዝግበዋል። በተያያዘም ምስክር ራሳቸው ትዕዛዝ ከሚሰጧቸው አልማው እና ማርሸት ከሚባሉት ግለሰብ ጋር የሚገናኙባቸውን የስልክ አድራሻ፣ የመኖሪያ አድራሻ እና የፎቶ ማስረጃዎች በፖሊስ ያስዩዙኛል በሚል ፍራቻ ድርጊቱ በተፈፀመ ማግስት ፎርማት ማድረጋቸውን ለችሎቱ ተናግረዋል። ችሎቱ የዐቃቤ ሕግ ስድስተኛ ምስክር ለመስማት መዝገቡ በይደር ተሻግሯል።

Add a review

The comment language code.

Restricted HTML

  • Allowed HTML tags: <a href hreflang> <em> <strong> <cite> <blockquote cite> <code> <ul type> <ol start type> <li> <dl> <dt> <dd> <h2 id> <h3 id> <h4 id> <h5 id> <h6 id>
  • Lines and paragraphs break automatically.
  • Web page addresses and email addresses turn into links automatically.