ፍርድ ቤቱ በእነ እስክንድር ነጋ ምስክር አሰማም ሒደት ላይ ክርክር ለማድረግ ተጨማሪ የውሳኔ ቀጠሮ ሰጠ

  • ስንታየሁ ቸኮል ፀበል ማረሚያ ቤት እንዲገበላቸው ጠይቀው በፍርድ ቤቱ ተፈቅዶላቸዋል።

ግንቦት 9፤ 2013 - የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አንደኛ ሕገ መንግሥታዊ እና የፀረ ሽብር ጉዳዮች ችሎት በዛሬው ችሎት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ ተቀብሎ ምስክር ለማድመጥ የቀጠረ ቢሆኖም፥ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የምስክር  አሰማም ሒደቱን በሚመለከት በድጋሚ በከፍተኛ ፍርድ ቤት ክርክር እንዲያደርጉ የሚል ትዕዛዝ በማስተላለፉ በከፍተኛው ፍርድ ቤት ምስክር ሳይደመጥ ቀርቷል።

እስክንድር ነጋን ጨምሮ ሁሉም ተከሳሾች በአካል በቀረቡበት በዚህ ችሎት፣ በበመዝገቡ ሁለተኛ ተከሳሽ የሆኑት ስንታየሁ ቸኮል፣ ለችሎቱ ጤናቸው በሚመለከት በሕክምና ከታዘዘላቸው መድኃኒት ውጪ በተጨማሪነት ፀበል መጠቀም ስለሚፈልጉ ችሎቱ ይህንን በሚመለከት ለማረሚያ ቤቱ እንደ ማንኛውም መድኃኒት ፀበል እንዲያስገቡላቸው ችሎቱ ትዕዛዝ እንዲሰጥላቸው አቤቱታ አቅርበዋል።

ችሎቱም ማንኛውም ዓይነት መድኃኒትም ይሁን ምግብ ተቀምሶ እንደሚገባ ሁሉ፣ ፀበሉም በዛ መልክ ይግባላቸው ሲል ትዕዛዝ ሰጥቷል።

ፍርድ ቤቱ መዝገቡን መርምሮ ምስክር የማሰማት ሒደቱ ላይ ክርክር መደረግ አለበት ወይስ የለበትም የሚለውን ለመወሰን ቀጣይ ቀነ ቀጠሮ ለግንቦት 17፤ 2013 ሰጥቷል።

Add a review

The comment language code.

Restricted HTML

  • Allowed HTML tags: <a href hreflang> <em> <strong> <cite> <blockquote cite> <code> <ul type> <ol start type> <li> <dl> <dt> <dd> <h2 id> <h3 id> <h4 id> <h5 id> <h6 id>
  • Lines and paragraphs break automatically.
  • Web page addresses and email addresses turn into links automatically.