የእንግዳውን ኪሳራ ማን ይክፈለው?

ጸሐፊ፡- ማሕሌት ፋንታሁን እንግዳው ዋኘው ይባላል፤ ትውልዱ እና ዕድገቱ በሰሜን ጎንደር ዞን፣ ታች አርማጭሆ ወረዳ ነው። የ33 ዓመት ወጣት ሲሆን፤ ከ1997 ወዲህ (በ1997፣በ2005 እና ከ2007—2009) ሦስት ጊዜ ለእስር ተዳርጓል። ከ1996 ጀምሮ በፖለቲካ ፓርቲ ውስጥ ገብቶ በመሳተፍ ትግል የጀመረው የቅንጅት አባል በመሆን ሲሆን አንድነት ፓርቲ በምዕራብ አርማጭሆ ሲመሠረት ደግሞ መሥራች አባል እና የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ በመሆን […]

Read More

ማንደፍሮ አካልነው፤ “ሚዲያ ስላወቀ እንጂ ሕይወትህ አትተርፍም ነበር ብለውኛል”

ጸሐፊ፡- በላይ ማናዬ በዓለም ዐቀፍ የቱሪስት መስህቧ ላሊበላ ከተማ ተወልዶ ያደገው ማንደፍሮ አካልነው፣ ከላሊበላ ተነስቶ ማዕከላዊ፣ ቃሊቲ፣ ቂሊንጦ እና ዝዋይ እስር ቤቶችን አዳርሷል፡፡ የ31 ዓመቱ ማንደፍሮ አካልነው ከስድስት ዓመታት በላይ እስር ቤት አሳልፏል፡፡ ‹ውጭ ሀገር ሆነው ነፍጥ አንስተው ኢትዮጵያን ከሚያተራምሱ ኃይሎች ጋር ግንኙነት አለህ› በሚል ግንቦት 17 ቀን 2003 ከሚኖርበት ላሊበላ ከተማ በፌደራል ፀረ-ሽብርተኝነት ግብረ […]

Read More

ተስፋሚካኤል አበበ፤ “ሆዴ ላይ ሲጋራ እየተረኮሱ ጠብሰውኛል”

ጸሐፊ፡- በላይ ማናዬ ተስፋሚካኤል አበበ ከጎንደር እስከ አዲስ አበባ በማሰቃያ እስር ቤቶች ውስጥ አልፏል፡፡ በቅፅል ሥሙ ህርያቆስ እየተባለ በወዳጆቹ ይጠራል፡፡ ከእስር ቤት የማይሽር ጠባሳ ይዞ የወጣው ተስፋሚካኤል የ28 ዓመት ወጣት ሲሆን ነዋሪነቱ በአማራ ክልል ጎንደር ከተማ ነው፡፡ ተስፋሚካኤል በፖሊስ ማቆያ ቦታዎች የደረሰበትን የሰብአዊ መብቶች ጥሰት እንደሚከተለው አጫውቶናል፡፡ ጎንደር 6ተኛ ፖሊስ ጣቢያ ከ2008 ክረምት ወራት ጀምሮ […]

Read More

ያሬድ ሑሴን – ከቂሊንጦ ቃጠሎ እስከ ሸዋ ሮቢት ስቃይ

ጸሐፊ፡- አጥናፉ ብርሃኔ በነሐሴ 26፤2008 በቂሊንጦ የእስረኞች ማቆያ ማረሚያ ቤት ውስጥ ከእስረኛ ቤተሰቦች ምግብ እንዳይገባ መደረጉ በእስር ቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ መናፈስ ጀመረ። ጉዳዩ ያሳሰባቸው ታራሚዎች በየክፍሉ የሚገኙ የእስረኛ ተወካዮችን ጉዳዩን እንዲያጣሩላቸው ቢጠይቁም ከማረሚያ ቤቱ አስተዳደሮች በቂ ምላሽ ሳያገኙ ቀሩ። ነሐሴ 28፣2008 የእስር ቤቱ አላፊዎች በለጠፉት ማስታወቅያ “የአተት ወረርሽኝ በማረሚያ ቤቱ በመግባቱ ከቤተሰብ ለእስረኛው የሚገባ […]

Read More

የጫልቱ ታከለ ፈተና እና ፅናት

ጸሐፊ፡- ማሕሌት ፋንታሁን ከአንዴም ሁለት ጊዜ የእስርን ሕይወት ተጋፍጣለች፡፡ በማዕከላዊ እና የትነቱ በማይታወቅ የእስር ቦታ የማሰቃየት ተግባር ተመሥርቶባታል፡፡ ከ8 ዓመታት በላይ ከዕድሜዋ ላይ ተቆጦ በእስር ባክኗል፡፡ ጫልቱ ታከለ፡፡ እርሷ ግን በፅናት ፈተናዋን ተወጥታለች፡፡ በእስር ቤት ውስጥ ከአስቸጋሪ ሁኔታዎች እና ክልከላዎች ጋር እየታገለች የመጀመሪያ ዲግሪዋን እስከመያዝ ደርሳለች፡፡ በዚህ ትረካ የጫልቱ ታከለን ያለፉት ዐሥር ዓመታት ጉዞ በወፍ […]

Read More