ጋዜጠኛ ጌጥዬ ያለው ችሎት በመድፈር የሁለት ወር የእስራት ቅጣት ተጣለባቸው

ጥቅምት 23፣ 2014 – የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ የፀረ ሽብርና  ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች ወንጀል ችሎት መዝገቡ የተቀጠረው ጌጥዬ ላይ ቅጣት ለማሳረፍ እና የዐቃቤ ሕግ ምስክር ለማሰማት ነው። የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት በእነ እስክንድር ነጋ የክስ መዝገብ የችሎት አዘጋገብ በተያያዘ ጌጥዬ ያለውን ችሎት በመድፈር ፍርድ ቤቱ ጥፋተኛ ብሎት የነበረ መሆኑ ይታወሳል። ፍርድ […]

Read More

የአዲስ ዓመት የሰላም ጥሪ – ከአገር በቀል የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች

ባሁኑ ወቅት አገራችን ኢትዮጵያ በከባድ ቀውስ ውስጥ ትገኛለች። በትግራይ፣ በአማራ፣ በምዕራብና ደቡብ ኦሮሚያ፣ በሶማሊ፣ በአፋር፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልሎች በሚካሔዱ ግጭቶች ምክንያት በሺሕ የሚቆጠሩ ወገኖቻችን እየሞቱ ነው። በመቶ ሺሕዎች የሚቆጠሩ ከቀያቸው እየተፈናቀሉ ነው። ሚሊዮኖች የአስቸኳይ ጊዜ ዕርዳታ ላይ ጥገኛ እየሆኑ ነው። ሕፃናት ልጆቻችን፣ በዕድሜ የገፉ ወገኖቻችን እና ሴቶቻችን በተለየ ሁኔታ ለመከራ ተጋላጭ […]

Read More

ፍርድ ቤቱ በእነ እስክንድር ነጋ መዝገብ የምስክሮች ደኅንነት ጥበቃ በተመለከተ ጉዳዩ ውስብስ ነው ሲል ብይን ለመስጠት ከምርጫ በኋላ ቀጠሮ ይዟል

ግንቦት 23፣2013 – የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አንደኛ የፀረ ሽብር እና ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች ችሎት እስክንድር ነጋን ጨምሮ ሁሉም ተከሳሾች ቀርበዋል። በዕለቱ በሁለቱም ወገን የምስክር ደኅንነት ጥበቃን በሚመለከት ክርክር በጽሑፍ ለችሎቱ የቀረበ ቢሆንም በተከሳሾች ጥያቄ መሠረት ፍርድ ቤቱ የቃል ክርክር እንዲደረግ ፍቃድ ሰጥቷል። ዐ/ሕግ በአዋጅ 699/2003 አንቀጽ 24 መሠረት 5 ምሰክሮች ከመጋረጃ ጀርባ […]

Read More

Photo Credit - Addis Standard

በእነ ጃዋር መሐመድ መዝገብ የዐቃቤ ሕግ ምስክሮች ከመጋረጃ ጀርባ እንዲታዩ የቀረበው ይግባኝ ተከሳሾች በሌሉበት ተደመጠ

ተከሳሾች በአካል ካልሆነ በቀር በፕላዝማ አንቀርብም ብለዋል። ዐቃቤ ሕግ ምስክሮች ጥበቃ እንደሚያስፈልጋቸው የመወሰን ሥልጣን የፍርድ ቤት ሳይሆን የዐቃቤ ሕግ ነው ብሎ ተከራክሯል። ሚያዝያ 20፤ 2013 – የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አንደኛ ሕገ መንግሥታዊ እና የፀረ ሽብር ጉዳዮች ችሎት፣ ምስክሮች ሥማቸው ሳይገለጽ በግልጽ ችሎት እንዲመሰክሩ የሰጠውን ብይን ተከትሎ ዐቃቤ ሕግ የምስክር ደኅንነት ጥበቃ ዐዋጁን […]

Read More

Photo Credit - Addis Standard

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በእነ ጃዋር መሐመድ ላይ የዐቃቤ ሕግ ምስክሮች በግልጽ ችሎት እንዳይሰሙ አገደ

ሚያዝያ 1፣ 2013 – የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ የፀረ ሽብር እና የሕገ መንግሥት ጉዳዮች ወንጀል ችሎት የተከሳሾች መብትን የሚያጣብብ ስለሆነ ምስክሮች በዝግ ችሎት ሊሰሙ አይገባም በማለት፣ የዐቃቤ ሕግ በምስክር ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 699/2003 መሠረት 146 ምስክሮቼ በየደረጃው በዝግ ችሎት ‘ከመጋረጃ በስተጀርባ ምስክርነታቸው ይሰማልኝ’ ብሎ ያቀረበውን አቤቱታ ውድቅ ማድረጉ ይታወሳል። ይሁንና በውሳኔው ቅር የተሰኘው ዐቃቤ […]

Read More