የእነ ጉርሜሳ አያኖ መዝገብ በተያዘው ቀጠሮ ምስክሮች ሰይደመጡ ቀሩ። (ጥቅምት 28 ፣2010)

* ችሎቱ ምስክሮች በተከሳሾች እና ዳኞች አለመግባባት ተቋርጧል። የእነ ጉርሜሳ አያኖን መዝገብ ለዛሬ ጥቅምት 28 ፣ 2010 የተቀጠረው ከአንደኛ እሰከ አራተኛ ካሉት ተከሳሾች ውጪ ያሉ ተከሳሾችን መከላከያ ምስክሮች ለመስማት በሚል ነው። በጠዋቱ ችሎት ዳኞች ሌሎች መዝገቦችን ሲሰሩ ስለነበር ቀጠሮው ወደ ከሰአት ዞሯል። ተከሳሾቹ የሚመገቡትን ምሳ በተመለከተ ጠበቃ አቶ ወንድሙ ኢብሳ ዳኞቹን ለማረሚያ ቤት ሃላፊዎች ትእዛዝ […]

Read More

በእነ ጉርሜሳ አያኖ መዝገብ ለመከላከያ መስክርነት የተጠሩ ባለስልጣናት ሳይቀርቡ ቀሩ፡፡ (ጥቅምት 27፣ 2010)

“ለምስክርነት የተዘረዘሩት ባለ ስልጣናት መጥሪያ አልተላከላቸውም፡፡” ፍርድ ቤቱ “ከተከበሩ አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ጋር አንድ ላይ የምክር ቤት አባል ነበርን፡፡ እሳቸው ኢህአዴግ ስለሆኑ ጠቅላይ ሚኒስቴር ሆኑ እኔ ተቃዋሚ ስለሆንኩ እስር ቤት ገባሁ፡፡” ሁለተኛ ተከሳሽ አቶ ደጀኔ ጣፋ  “እኔ በተሰጠው ቀጥሮ (ህዳር 6) ልቀርብ ፈቃደኛ አይደለሁም፡፡ ከህግ በላይ የሆኑ ሰዎች አሉ ማለት ነው? በፍርድ ቤቱ አካሄድ   አላመንኩበትም፡፡” […]

Read More

አክቲቪስት ዮናታን ተስፋየ የይግባኝ አቤቱታ በሰበር ክርክሩን አሰምቷል (ጥቅምት 24/2010 )

ማህበራዊ ሚዲያ በተለይም ፌስ ቡክ ላይ በጻፋቸው ጽሁፎቹ ምክንያት የሽብር ወንጀል ፈጽመሃል በሚል የስድስት አመት ከስድስት ወር እስራት የተፈረደበት የሰማያዊ ፓርቲ የቀድሞው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አክቲቪስት ዮናታን ተስፋዬ ዛሬ ጥቅምት 24/2010 ዓ.ም የፌደራል ጠ//ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ወንጀል ችሎት የይግባኝ አቤቱታ ክርክር አሰምቷል፡፡ አቶ ዮናታን ተስፋዬ ይግባኝ አቤቱታ ያቀረበው በስር ፍርድ ቤት (ከ/ፍ/ቤት ልደታ 4ኛ ወንጀል […]

Read More

አቶ ማሙሸት አማረ ያቀረቡት የክስ መቃወሚያ ሙሉው ውድቅ ተደርጓል:: (ጥቅምት 24/2010)

የሽብር ክስ የቀረበባቸው የመኢአድ የቀድሞው ፕሬዚዳንት አቶ ማሙሸት አማረ ጥቅምት 13/2010 ዓ.ም ለፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት ያቀረቡት አራት ገጽ የመጀመሪያ ደረጃ የክስ መቃወሚያቸው ሙሉ በሙሉ ውድቅ ተደርጓል፡፡ ዛሬ ጥቅምት 24/2010 ተከሳሹ ቀደም ብለው ባቀረቡት መቃወሚያ ላይ ብይን የሰጠው ፍ/ቤቱ የተከሳሽን መቃወሚያ ሙሉውን ሳይቀበለው ቀርቷል፡፡ አቶ ማሙሸት የቀረበባቸው የሽብረተኝነት ክስ ግልጽ አለመሆኑን […]

Read More

ዶ/ር መረራ ጉዲና ላይ ሁለት የደረጃ ምስክሮች ተሰምተዋል:: (ጥቅምት 24/2010 ዓ.ም )

በእነ ዶ/ር መረራ ጉዲና የክስ መዝገብ 1ኛ ተከሳሽ በሆኑት ዶ/ር መረራ ላይ ሁለት የአቃቤ ህግ የደረጃ ምስክሮች ዛሬ ጥቅምት 24/2010 ዓ.ም የፌደራል ከፍተኛው ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት ተሰምተዋል፡፡ ከሳሽ የፌደራል አቃቤ ህግ በአጠቃላይ አራት የደረጃ ምስክሮችን በ1ኛ ተከሳሽ ዶ/ር መረራ ጉዲና ላይ እንዳቀረበ ከችሎቱ የተገለጸ ሲሆን፣ በዛሬው ውሎ ምስክሮቹ ቀርበው ከመሰማታቸው በፊት ምስክሮቹ […]

Read More