በእነ እስክንድር ነጋ መዝገብ ቀሪ የዐቃቤ ሕግ ምስክሮችን ለመስማት ለሦስተኛ ግዜ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጠ

ሕዳር 7፣ 2014 - ፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ የፀረ ሽብርና ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች ወንጀል ችሎት በእነ እስክንድር መዝገብ የተቀጠረው በኮሮና ተይዞ ያገገመውን የዐቃቤ ሕግ ምስክር ለማድመጥ እና የአስካል ደምሌ አቤቱታ ላይ ምላሽ ለመስጠት ነው።

የዐቃቤ ሕግ ምስክር የሆኑት ግለሰብ በሕዳር 6፣ 2014 በዋለው ችሎት ዐቃቤ ሕግ እንደገለጸው በኮሮና በሽታ ታመው እንደነበር አሁን ግን የተሻላቸው ስለሆነ ሕዳር 7 በሚውለው ቀጠሮ መጥተው ምስክርነታቸውን እንደሚሰጡ ማሳወቁ የሚታወስ ነው። ይሁንና  ሕዳር 7 በዋለው ችሎት ዐቃቤ ሕግ "ለምስክሩ ደውዬ አሞኝ ሆስፒታል ሄጃለው መምጣት አልችልም" ብለውኛል በዚህ ምክነያት ምስክሩን ማቅረብ አልቻልኩም፤ ቀሪ ሌሎች ምስክሮች እየተሰሙ እሳቸው በተለዋጭ ቀጠሮ የሕክምና ማስረጃቸውን ይዘው እንዲቀርቡ ይደረጋል ብሏል።

ይህን ተከትሎ ተከላካይ ጠበቆች በበኩላቸው ምስክሩ ከበሽታው ያገገሙ ስለሆኑ ቀርበው መመስከር ይችላሉ የሚል ማረጋገጫ ዐቃቤ ሕግ ለፍርድ ቤት ሰጥተው እንደነበር ይታወሳል። በዚህ ችሎት ደግሞ ማቅረብ አልቻሉም። በተጨማሪም መታመማቸውን የሚያስረዳ ማስረጃም አላቀረቡም። ስለዚህ በሥነ ስርዓት ሕገ መሠረት ቀጠሮ ለማራዘም በቂ ምክንያት ስላልሆነ ፍርድ ቤቱ አቤቱታውን ውድቅ አድርጎ ምስክሩ እንዲታለፍ በማለት ምላሽ ሰተውበታል።

በመዝገቡ ሁለተኛ ምስክር የሆኑት ስንታየሁ ቸኮል በተጨማሪ "እኔም ሕመሜን ችዬ መድኃኒት ይዤ ነው የምመጣው። ይሄ ሁሉ የተፋጠነ ፍትሕ ለማግኘት ነው፤ እንዲህ ያለው አሳዛኝ ነገር በእኛ ላይ ለምን ይደረጋል? ዐቃቤ ሕግ ሆን ብሎ እያስተጓጎለ ነው። ስለዚህ ችሎቱ ይህን ተመልክቶ መፍትሔ ይስጠን” ሲሉ ፍርድ ቤቱን ጠይቀዋል።

የግራ ቀኙን ክርክር ያደመጠው ችሎት 4ኛ ተከሳሽ በሚመለከት በፍርድ ቤት መጥሪያ የሕክምና ማስረጃቸው በመያዝ ከተቀሩት ምስክሮች ጋር ሕዳር 9፣ 2014 ቀርበው  እንዲመሰክሩ አዟል። በተጨማሪም ችሎቱ አራተኛ ተከሳሽ የሆኑት አስካል ደምሌ ከእናታቸው ጋር በሳምንት አንድ ቀን ለ10 ደቂቃ በስልክ እንዲገናኙ አዟል።

Add a review

The comment language code.

Restricted HTML

  • Allowed HTML tags: <a href hreflang> <em> <strong> <cite> <blockquote cite> <code> <ul type> <ol start type> <li> <dl> <dt> <dd> <h2 id> <h3 id> <h4 id> <h5 id> <h6 id>
  • Lines and paragraphs break automatically.
  • Web page addresses and email addresses turn into links automatically.