በእነ እስክንድር ነጋ መዝገብ ፖሊስ የዐቃቤ ሕግ ምስክሮችን በአድራሻቸው ማግኘት አልቻልኩም አለ

ሕዳር 9፣ 2014 - መዝገቡ የተቀጠረው የዐቃቤ ሕግ ምስክሮችን ለማድመጥ ቢሆንም እንኳን ምስክሮች ግን ሳይቀርቡ ቀርተዋል። መጥሪያውን እንዲያደርስ የታዘዘው የፌደራል ፖሊስ ምስክሮቹ ከዚህ በፊት ሰጥተውት በነበረው አድራሻዎቻቸው መካከል የአንዱን ምስክር ብቻ በአድራሻቸው አግኝቶ የፍርድ ቤት መጥሪያውን መስጠት እንደቻለ እና ለተቀሩት ሁለት ምሰክሮች ግን የፍርድ ቤት መጥሪያውን በአድራሻቸው መስጠት እንዳልቻለ ለችሎቱ በጽሑፍ አቅርቧል። ይህን ተከትሎ ዐቃቤ ሕግ ተለዋጭ ቀጠሮ እንዲሰጠው ፍርድ ቤቱን ጠይቋል።

ተከላካይ ጠበቆች በበኩላቸው የዐቃቤ ሕግ ምስክሮች በሰጡት አድራሻ መገኘት ባልቻሉበት ሁኔታ ቀጠሮ መሰጠት የለበትም፤ ምክንያቱም እነኚህ ምስክሮች እንዲቀርቡ ከሦስት ግዜ በላይ ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል፤ ችሎቱ ከዚሀ በኋላ ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱ የተከሳሾችን መሠረታዊ መብቶች ላይ ተጨማሪ ጥሰት እንዲፈፀም ዕድል መስጠት ነው የሚሆነው፤ በተጨማሪም ፖሊስ ባስረዳው መሠረት ምስክሮቹን ማቅረብ እንደማይችል ስለሆነ "የምንረዳው" ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱ ሥነ ስርዓታዊ አይደለም ሲሉ ተከራክረዋል።

በዚሁ ሐሳብ ላይ ዐቃቤ ሕግ፣ ምስክሮች መቅረብ የማይችሉ ከሆነ በምን መልኩ እንደሚቀርቡ ግልጽ በሆነበት በፍፁም መቅረብ አይችሉም የሚል ዕሳቤ መወሰዱ ተገቢ አይደለም በማለት ፖሊስ ሊያገኛቸው አይችልም የሚያስብል ምክንያታዊ ሁኔታ አለመሆኑን ለችሎቱ በማስረዳት በተከላካይ ጠበቆች ለተነሳው አቤቱታ ምላሽ ሰጥተውበታል። የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ የፀረ ሽብርና ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች ወንጀል ችሎት በእነ እስክንድ ነጋ መዝገብ   በጠበቆች በኩል የቀረበውን አቤቱታ እና በዐቃቤ ሕግ የተሰጠውን ምላሽ መርምሮ ትዕዛዝ  ሰጥቷል። በአድራሻቸው የተገኙት የዐቃቤ ሕግ ምስክር በነገው ዕለት ቀርበው የምስክርነት ቃላቸውን እንዲሰጡ እና የተቀሩት ምስክሮች በሚመለከት ትዕዛዝ ለመስጠት መዝገቡን በይደር ቀጥሯል።

Add a review

The comment language code.

Restricted HTML

  • Allowed HTML tags: <a href hreflang> <em> <strong> <cite> <blockquote cite> <code> <ul type> <ol start type> <li> <dl> <dt> <dd> <h2 id> <h3 id> <h4 id> <h5 id> <h6 id>
  • Lines and paragraphs break automatically.
  • Web page addresses and email addresses turn into links automatically.