Skip to main content

ካርድ 'በቴክኖሎጂ የተደገፈ ፆታን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶች' የሚዳስስ ጥናት ይፋ ማድረጊያ ዐውደ ርዕይ ላይ ተሳተፈ

የመብቶች እና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል (ካርድ) ሴንተር ፎር ኢንፎርሜሽን ሪዚሊየን (CIR) የተባለ ዓለም ዐቀፍ ተቋም፣ በኢትዮጵያ 'በቴክኖሎጂ የተደገፈ ፆታን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶች' የሚዳስስ ጥናት ይፋ ማድረጊያ መርሐ ግብርን፣ ከኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል (EHRDC) ጋር በመሆን ትላንት፣ ግንቦት 1፣ 2016፣ በኤሊያና ሆቴል የተዘጋጀው ዐውደ ርዕይ ላይ ተሳትፎ አድርጓል።

ካርድ በዲጂታል መብቶች ፕሮግራሙ ሥር ፍትሐዊ የበይነመረብ ተደራሽነት እንዲስፋፋ እና የበይነመረብ ተጠቃሚዎች ደኅንነት እንዲረጋገጥ የሚያስችሉ ሥራዎችን ይሠራል። ካርድ በዐውደ ርዕዩ ላይ ተሳትፎ ሲያደርግ በቴክኖሎጂ የተደገፈ ፆታን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶች ለበይነመረብ ተጠቃሚዎች ደኅንነት ዋነኛ ስጋት መሆኑን ስለሚያምን ነው። 

ካርድ በተከታታይ ዘመቻ ከሚያደርግባቸው ጉዳዮች መካከል፣ #KeepItSafe በሚል ሀሽታግ ሥር መንግሥት እና ማኅበራዊ ሚዲያዎችን ጨምሮ፣ ሁሉም ባለድርሻ አካላት፣ የበይነመረብ ተጠቃሚዎችን ደኅንነት እንዲጠብቁ መሟገት አንዱ ነው። ለዚህ ዐውደ ርዕይ ሲባል፣ ካርድ በይነመረብ ላይ በሠራው ሰርቬይ እንደተረዳው 78% የሚሆኑት እና ቴክኖሎጂ ላይ ፆታን መሠረት ያደረገ ጥቃት የደረሰባቸው ሴቶች፣ ጥቃቱን ሪፖርት አያደርጉም። 

ከሰርቬዩ በተጨማሪም፣ ካርድ ቴክኖሎጂ ያመጣው ፆታዊ ጥቃትን ለመረዳት እና ለመመከት የሚያስችል መረጃ የያዘ ብሮሸር ለታዳሚዎች አከፋፍሏል።

በዐውደ ርዕዩ ላይ፣ የካርድ ተሳትፎ፣ ድርጅታችን ለዲጂታል መብቶች እና ደኅንነት ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይበት ነው። የሰርቬዩ ግኝትም በቴክኖሎጂ የተደገፉ ፆታዊ ጥቃቶች እምብዛም ሪፖርት እንደማይደረጉ በማሳየቱ የሁላችንንም ርብርቦሽ የሚጠይቅ ሥራ ከፊታችን እንደተደቀነ ማስታወሻ ነው። 

Share this post

Comments (0)

Add new comment

The comment language code.

Restricted HTML

  • Allowed HTML tags: <a href hreflang> <em> <strong> <cite> <blockquote cite> <code> <ul type> <ol start type> <li> <dl> <dt> <dd> <h2 id> <h3 id> <h4 id> <h5 id> <h6 id>
  • Lines and paragraphs break automatically.
  • Web page addresses and email addresses turn into links automatically.