ዐቃቤ ሕግ በእነ እስክንድር ነጋ መዝገብ የምስክሮቼ የሥም ዝርዝር በሚዲያ እንዳይቀርብ ሲል ያስገባው አቤቱታ በፍርድ ቤቱ ውድቅ ተደረገ

ጥቅምት 9፣ 2014 - የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት፣ ልደታ ምድብ፣ አንደኛ የፀረ ሽብር እና ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች ችሎት በቀደመው ችሎት ላይ ዐቃቤ ሕግ በእነ እስክንድር ነጋ ላይ የሚቀርቡ 21 ምስክሮችን ሥም ዝርዝር በሚዲያ እንዳይቀርብ አቤቱታ በጽሑፍ ማስገባቱ የሚታወስ ነው። ይህን ተከትሎ ፍርድ ቤቱ በጉዳዩ ላይ ሁለቱንም ወገን አከራክሮ ዐቃቤ ሕግ ያቀረበውን አቤቱታ ውድቅ አድርጎታል።

በዛሬው ችሎት ላይ ዐቃቤ ሕግ ከዘጠኝ ምስክሮች ውጪ ያሉ ምስክሮቼ መመስከር እንደሚፈልጉ ፍቃዳቸውን ጠይቀን ከተስማሙ የምናመጣቸው ይሆናል በማለት የዘጠኙን ምስክሮች ሥም ዝርዝር ለፍርድ ቤቱ አቅርቧል።

ፋንታሁን አሰፋ፣ መንበረ በቀለ፣ ወርቁ ታደሰ፣ ፍፁም ታደሰ፣ ደረጀ ግዛው፣ ቴዎድሮስ ለማ፣ ያየህ ብርሃኑ፣ ጌትነት ተስፋዬ፣ እና ትንሳዬ ማሞ ዐቃቤ ሕግ ከ21 ምስክሮች ውስጥ የሥም ዝርዝራቸውን ያቀረባቸው ምስክሮች ሲሆን፥ ከእነዚህ ውስጥ ነገ ሁለቱ ይመሰክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ፍርድ ቤቱ የተቀሩት ዐሥራ ሁለት ምስክሮች አቃቤ ሕግ የሥም ዝርዝራቸውን አሟልቶ በነገው ዕለት እንዲያቀርብ እና ምስክር እንዲያሰማ ትዕዛዝ ሰጥቷል።

Add a review

The comment language code.

Restricted HTML

  • Allowed HTML tags: <a href hreflang> <em> <strong> <cite> <blockquote cite> <code> <ul type> <ol start type> <li> <dl> <dt> <dd> <h2 id> <h3 id> <h4 id> <h5 id> <h6 id>
  • Lines and paragraphs break automatically.
  • Web page addresses and email addresses turn into links automatically.