ፍርድ ቤቱ በእነ እስክንድር ነጋ መዝገብ ቀሪ የዐቃቤ ሕግ ምስክሮችን ከሕዳር 6-10 ለመስማት ቀጠሮ ሰጠ

ጥቅምት 26፣ 2014 - የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ የፀረ ሽብርና ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች ወንጀል ችሎት በእነ እስክንድ ነጋ መዝገብ  ዐቃቤ ሕግ ያቀረበውን አቤቱታ እና በጠበቆች በኩል የተሰጠውን ምላሽ መርምሮ ብይን ሰቷል።

 

የታመመው 4ኛ ምስክር በሚመለከት የሕክምና ማስረጃ ይዞ በመቅረብ መመስከር እንደሚችል፤ 8ኛ እና 9ኛ ምስክሮች በፍርድ ቤቱ በኩል መጥሪያ እንዲደርሳቸው አዟል። በተጨማሪም ማንነታቸው ያልተገለጹት 12 ምስክሮች ማንነታቸው በግልጽ እንዲቀርብ እና ከቀሪ ሦስቱ ምስክሮች ጋር ከሕዳር 6-10 ዐቃቤ ሕግ እንዲያስመሰክር ፍርድ ቤቱ አዟል።

 

ከዚህ መዝገብ ጋር ተያይዞ በባልደራስ የፌስቡክ ገጽ የችሎት ዘገባ ላይ በሚለጠፉ ጽሑፎች የሚሰጡ አስተያየቶች ላይ በምስክሮች ላይ ዛቻ እና ስድብ እየደረሰ ነው፤ ስለዚህ በቀጣይ የሚቀርቡ ምስክሮች ማንነት በሚዲያ እንዳይገለጽ በማለት 10/02/2014 ዐቃቤ ሕግ ያቀረበውን አቤቱታ ፍርድ ቤቱ፣ አስተያየት ሰጪዎች የባልደራስ አባላት እና ደጋፊዎች ወይንም ተቃዋሚዎች ይሁኑ ባልተለዩበት ሁኔታ፣ በዐቃቤ ሕግ በኩልም ይህን የሚያስረዳ መረጃ ባለመቅረቡ ሲል ችሎቱ የዐቃቤ ሕግን አቤቱታ ውድቅ አድርጎታል።

 

አስካል ደምሌ በስልክ ቤተሰቦቼን ማግኘት ይፈቀድልኝ ሲሉ ያቀረቡትን አቤቱታ ችሎቱ ማረሚያ ቤቱ አስተያየት ይዞ ለሕዳር 1 እንዲቀርብ አዟል።

Add a review

The comment language code.

Restricted HTML

  • Allowed HTML tags: <a href hreflang> <em> <strong> <cite> <blockquote cite> <code> <ul type> <ol start type> <li> <dl> <dt> <dd> <h2 id> <h3 id> <h4 id> <h5 id> <h6 id>
  • Lines and paragraphs break automatically.
  • Web page addresses and email addresses turn into links automatically.