ዐቃቤ ሕግ በእነእስክንድር ነጋ መዝገብ ምስክሮቼን በኢ-መደበኛ መንገድ ማግኘት ስላልቻልኩ በፍርድ ቤት መጥሪያ ይጠሩልኝ አለ

ጥቅምት 25፣ 2014 - የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ የፀረ ሽብርና ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች ወንጀል ችሎት መዝገቡ የተቀጠረው ከባለፈው የቀጠለ የዐቃቤ ሕግ ምስክር ለማሰማት ነው።

የዐቃቤ ሕግ ስድስተኛ ምስክር ከእስክንድር ተሰጥቷቸው የፈፀሟቸውን እና ያስፈፀማቸውን የድርጊት ማስረጃዎችን በሙሉ ሲያጠፉ የእስክንድርን ስልክ ያላጠፉት ሥማቸውን በኮድ ስለመዘገቡት እንደሆነ እና በክሱ ላይ የተጠቀሱት ተከሳሽ ቀለብ ሥዩምን እና አስካል ደምሌን የባልደራስ አመራር ከመሆናቸው ውጪ ምንም ዓይነት ድርጊት ሲፈፅሙም ሆነ ትዕዛዝ ሲሰጡ አለማየታቸውን መስክረዋል። እንዲሁም ምስክርነት የሰጠባቸውን ጉዳዮች በሙሉ ሲፈፅም የነበረው ሥልጣን አገኛለሁ በሚል ተስፋ መሆኑን ጨምረው ገልጸዋል።

ከዘጠኙ የዐቃቤ ሕግ ምስክሮች ቀሪ ሦስት ምስክሮች በችሎት እንዲመሰክሩ ዳኞች ቢጠይቁም ዐቃቤ ሕግ ግን አራተኛ ምስክራቸው በኮሮና ምክንያት መምጣት አለመቻላቸውን እና ድነው በሚወጡበት ወቅት ማስረጃ እንደሚያቀርቡ፣ 8ኛ እና 9ኛ ምስክሮች ደሞ በኢ-መደበኛ መንገድ ማግኘት ስላልቻልኩ ፍርድ ቤቱ መጥሪያ ትዕዛዝ ይስጠን በማለት ዐቃቤ ሕግ ፍርድ ቤቱን ተለዋጭ ቀጠሮ ጠይቋል።

ጠበቆች በበኩላቸው የዐቃቤ ሕግ ምስክራቸው የታመሙ ስለመሆናቸው ማስረጃ ባለማቅረቡ እና የተቀሩት ሁለቱ ምስክሮች ደሞ ዐቃቤ ሕግ ማግኘት ባልቻለበት ሁኔታ በፍርድ ቤት መጥሪያ ይጠሩልኝ ማለት ተገቢ አይደለም ሲሉ ፍርድ ቤቱን በቀረቡት ምስክሮች መሠረት ብቻ ፍትሕ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል። በሌላ በኩል አስካል ደምሌ ከቤተሰብ ጋር የስልክ ግኑኝት ማድረግ እንዲችሉ ለማረሚያ ቤት ትዕዛዝ እንዲሰጥላቸው ለችሎቱ አቤቱታ አቅርበዋል። ፍርድ ቤቱ በቀረቡ አቤቱታዎች ላይ ትዕዛዝ ለመስጠት ለነገ ተቀጥሯል።

Add a review

The comment language code.

Restricted HTML

  • Allowed HTML tags: <a href hreflang> <em> <strong> <cite> <blockquote cite> <code> <ul type> <ol start type> <li> <dl> <dt> <dd> <h2 id> <h3 id> <h4 id> <h5 id> <h6 id>
  • Lines and paragraphs break automatically.
  • Web page addresses and email addresses turn into links automatically.