የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በእነ እክንድር ነጋ የክስ መዝገብ ምስክሮች በግልጽ ችሎት እንዲሰሙ ውሳኔ ሰጠ

ነሐሴ 10፣ 2013፤ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ የፀረ ሽብር እና የሕገ መንግሥት ጉዳዮች ወንጀል ችሎት በእነ እስክንድር መዝገብ ላይ ከዚህ ቀደም በነበረው ቀጠሮ በግልጽ ችሎት የዐቃቤ ሕግ ምስክሮችን ለመስማት የሰጠው ቀጠሮ ምስክር ሳይሰማ በዐቃቤ ሕግ ይግባኝ አቤቱታ በሰበር ሰሚ ችሎቱ ዕግድ መጣሉ ይታወሳል።

ዕግዱን ጥሎ የነበረው የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የተከሳሾችን መልስ እና ዐቃቤ ሕግ ያቀረበውን የመልስ መልስን መርምሮ ነሐሴ 10 ከሰዓት በኋላ በዋለው ችሎት የዐቃቤ ሕግን የይግባኝ አቤቱታ ውድቅ በማረግ በእነ እስክንድር መዝገብ ላይ የሚመሰክሩ ምስክሮች በግልጽ ችሎት እንዲሰሙ ሲል የታችኛውን ፍርድ ቤት ውሳኔ አጽድቋል። የከፍተኛው ፍርድ ቤት እስክንድር ነጋን ጨምሮ የአምስት ተከሳሾችን መደበኛ ጉዳይ ለማየት ለቅጥምት 04፣ 2014 ቀጠሮ መስጠቱ ይታወሳል።

Center for Advancement of Rights and Democracy (CARD)

Making Democracy the Only Rule of Game!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *