ዴሞክራሲን ብቸኛው የጫወታ ሕግ ማድረግ!
ሴንተር ፎር አድቫንስመንት ኦፍ ራይትስ ኤንድ ዴሞክራሲ (የመብቶች እና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል /ካርድ/)፣ ለትርፍ ያልተቋቋመ፣ በአዋጅ ቁጥር 1113/2011፣ በኢትዮጵያ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን መዝገብ ቁጥር 4307 ሐምሌ 17፣ 2011 የተመዘገበ፣ ቦርድ መር፣ የአገር በቀል የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅት ነው። ካርድ ሰብዓዊ መብቶች የተከበሩባት እና ዴሞክራሲያዊ ባሕል ያበበባት ኢትዮጵያን የማየት ራዕይ ሰንቆ፥ በኢትዮጵያ ለሰብዓዊ መብቶች መከበር እና ለዴሞክራሲያዊ ባሕል ግንባታ የተመቻቸ የሲቪክ፣ የሚዲያ፣ እና የዲጂታል ምኅዳር እንዲገነባ እየሠራ የሚገኝ ድርጅት ነው። ተጨማሪ ያንብቡ...
የካርድ ማንነት
ካርድ በሰብዓዊ መብቶች እሴቶች የታነፀ ግንዛቤ ማሳደግ፣ ማደራጀት፣ እና የፖለሲሲ ሙግት በማድረግ ዴሞክራሲያዊ የብዙኃን ባሕል እና ሕዝባዊ ንቅናቄን ለመፍጠር እየተጋ ያለ ድርጅት ነው።
የካርድ ራዕይ
ሰብዓዊ መብቶች የተከበሩባት እነ ዴሞክራሲያዊ ባሕል ያበበባት ኢትዮጵያን ማየት።
የካርድ ተልዕኮ
ለሰብዓዊ መብቶች መከበርና ዴሞክራሲያዊ ባሕል ግንባታ የተመቻቸ የሲቪክ፣ የሚዲያና፣ የዲጂታል ምኅዳር እንዲጎለበት መሥራት ነው።
የካርድ አንኳር ዓላማዎች
ካርድ፣ በሕግ የተመዘገበባቸው የሥራ ኃላፊነቶቹ የሚከተሉት ናቸው፦
- የዲሞክራሲ ዕሴቶችን በማስረፅ፣ ግንዛቤን በማሳደግና የዲሞክራሲ ልምምድ መድረኮችን በማዘጋጀት ዴሞክራሲያዊ ባሕል በኢትዮጵያ እንዲጎለብት መሥራት፣
- በመንግሥታዊ እና መንግሥታዊ ባልሆኑ ተቋማት ግልጽነት እና ተጠያቂነትን ለማጠናከር የሚያግዙ ወቅታዊ የመከታተል፣ የመሰነድ፣ ይፋ ማድረግ እና የሙግት ሥራዎችን መሥራት፣
- አስፈላጊ የሆኑ ለውጦችን ለማምጣት የፖሊሲ ጥናትና ምርምር እንዲሁም ምክክር እና ግፊት ማድረግ፣
- ለዴሞክራሲ ተቋማት ሙያዊ እና ቴክኒካዊ ድጋፍ ማድረግ፣
- የሰብዓዊ እና ዴሞክራሲያዊ መብቶች እንዲከበሩ የኢትዮጵያን ሕግ መሠረት በማድረግ የፖሊስ ማቆያዎችን፣ ማረሚያ ቤቶችን እና የፍርድ ቤት ሒደቶችን መከታተል፣ መሰነድ እና ሪፖርት ማውጣት፣
- የሚዲያ ምኅዳሩ እንዲሰፋ እና የጋዜጠኞች ሙያተኝነት ሥነ ምግባር እንዲጎለብት መሟገት እና የአቅም ግንባታ ድጋፍ ማድረግ፣
- የዲጂታል መብቶች እንዲከበሩ እና የዲጂታል ቴክኖሎጂ ተጠቃሚዎች ደኅንነት እንዲጠበቅ መሟገት እና ድጋፍ መስጠት፣
- ምርጫዎችን መታዘብ፣ የሥነ ዜጋ እና የመራጮች ትምህርት መስጠት።
Programs
-
የዜግነት ተሳትፎ
ካርድ ለሰብዓዊ መብቶች መከበር እና ለዴሞክራሲያዊነት የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች መበራከት እና መጠናከር ወሳኝ ነው ብሎ ያምናል። ይሁን እንጂ መደበኛ እና የተደራጁ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች የተሰባሰቡት መሐል አገር ነው። ስለሆነም፣ በዚህ መርሓግብር ሥር፣ በሁሉም የኢትዮጵያ አቅጣጫዎች የሚገኙ ኢ-መደበኛ እና ትውፊት ተኮር ተቋማትን ወደ መደበኝነት እንዲሁም በግለሰቦች ተነሳሽነት የተጀመሩ ንቅናቄዎች ወደ ተቋማዊነት እንዲያድጉ ለማድረግ የሚያስችሉ የአቅም ግንባታ ተከታታይ ሥራዎች፣ እንዲሁም የወጣቶች እና የሴቶችን አቅም እና ተሳትፎ የሚያጎለብቱ ሥራዎች ይከናወናሉ።
-
የሚዲያ ምኅዳር ዕድገት
ለዴሞክራሲያዊ ባሕል ግንባታ አስቻይ የሚዲያ ምኅዳር መኖር፣ የጋዜጠኞች ደኅንነት ሕጋዊ እና ተግባራዊ ጥበቃ ማግኘት፣ እንዲሁም ሙያተኝነት እና ሥነ ምግባር ማደግ ወሳኝ ናቸው። ስለሆነም፣ በዚህ መርሓግብር ሥር፣ ካርድ ከጋዜጠኞች፣ ከሚዲያ ተቋማት እና ማኅበራት ጋር በትብብር በመሥራት የጋዜጠኞች የወል የመደራደሪያ አቅም እንዲጎለበት፣ የሚዲያ ምኅዳሩ እንዲሠፋ፣ እና የሙያተኞቹ አቅም እንዲያድግ የሚያስችሉ ሥራዎች ያከናውናል።
-
የዲጂታል መብቶች
በኢትዮጵያ የበይነመረብ ተደራሽነት ዝቅተኛ ከመሆኑም በላይ የበይነመረብ ተጠቃሚዎቹ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አረዳድ ክኅሎታቸው ዝቅተኛ ነው። አልፎ ተርፎም፣ የበይነመረብ ተጠቃሚዎችን ደኅንነት ለማስጠበቅ የሚያስችሉ ሁለገብ ሕጋዊ ማዕቀፎች የሉም። ስለሆነም፣ ይህ መርሓግብር የበይነመረብ ተደራሽነት እንዲስፋፋ እና የበይነመረብ ዲጂታል ቴክኖሎጂ ተጠቃሚዎችን ነጻነት እና ደኅንነት እንዲጠበቅ የሙግት ሥራዎች ይከናወኑበታል።
-
የሕዝብ አስተዳደርና ዴሞክራሲያዊነት
ዴሞክራሲያዊነት ከታችኛው የአስተዳደር እርከን ጀምሮ ወደ ላይኛው የመንግሥት መዋቅር እንዲገነባ፣ የአስተዳደር መዋቅሮችን እና የአስተዳደር ዘይቤያቸውን ተከታታይ የሆነ ክትትል፣ ስነዳ፣ እና እወጃ ማድረግ ያስፈልጋል። ስለሆነም፣ ይህ መርሓግብር፣ በኢትዮጵያ ፌዴሬሽን ክልላዊ መስተዳድሮችን እና የፌዴራል ከተማ መስተዳድሮችን አስተዳደር በዴሞክራሲያዊነት የአስተዳደር መርሖዎች በመገምገም እንዲሻሻሉ በማስረጃ የተደገፈ የሕግ፣ ፖሊሲ እና አተገባበር ሙግት ሥራዎች ይከናወኑበታል።