ፍርድ ቤቱ በእነ እስክንድር ነጋ መዝገብ የምስክሮች ደኅንነት ጥበቃ በተመለከተ ጉዳዩ ውስብስ ነው ሲል ብይን ለመስጠት ከምርጫ በኋላ ቀጠሮ ይዟል

ግንቦት 23፣2013 - የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አንደኛ የፀረ ሽብር እና ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች ችሎት እስክንድር ነጋን ጨምሮ ሁሉም ተከሳሾች ቀርበዋል።

በዕለቱ በሁለቱም ወገን የምስክር ደኅንነት ጥበቃን በሚመለከት ክርክር በጽሑፍ ለችሎቱ የቀረበ ቢሆንም በተከሳሾች ጥያቄ መሠረት ፍርድ ቤቱ የቃል ክርክር እንዲደረግ ፍቃድ ሰጥቷል።

ዐ/ሕግ በአዋጅ 699/2003 አንቀጽ 24 መሠረት 5 ምሰክሮች ከመጋረጃ ጀርባ እንዲመሰክሩ የጠየኩት የዐ/ሕግ ክስ ላይ የሚታየው ሁለኛው ክስ ልዩ ሥልጠና በመውሰድ በግለሰቦች ላይ ጥቃት የሚደርሰ ድርጊት በመሆኑ ይህ ለዐ/ሕግ የስጋት ምክንያት ስለሆነ በምስክሮች አና በቤተሰቦቻቸው ላይ የጥቃት ጉዳት ይደርሳል የሚል ስጋት ስላለባቸው እንደሆነ ለችሎቱ አሳውቀዋል።

በተጨማሪም የተከሳሽ ደጋፊዎች ምስክሮቹ ላይ የአካል ጉዳት ጥቃት ለማድረስ እንደሞከሩባቸው ለዐ/ሕግ ጽ/ቤት ድረስ በመቅረብ ምስክሮቹ የደኅነንት ስጋት እንዳለባቸው አሳውቀዋል። ስለዚህ ፍ/ቤቱ የምስክሮችን የደኅንነት ስጋት በልዩ ሁኔታ ከግንዛቤ በማስገባት፣ በልዩ ትኩረት አሁንም ስጋቶችን አረጋግጦ በዝግ ችሎት እና ከማጋረጃ ጀርባ ምስክሮች የሚደመጡበትን ሁኔታ ያረጋጥ በማለት ዐ/ሕግ አሳስበዋል።

ፍርድ ቤቱም ዐ/ሕግ 16 ምስክሮች በዝግ ችሎት ይመስክሩ ያላቸውን በተከሳሾች ይታወቃሉ? በተጨማሪም አንድ ምስክር የዛቻ እና የሽጉጥ ተኩስ ሙከራ የደረሰበት ምስክር ስጋት እንዴት ነው? በማለት ለዐቃቤ ሕግ ጥያቄ አቅርቧል። ዐ/ሕግም እነዚህን ጉዳዮች “ፍርድ ቤቱ አጣርቶ እውነታውን ማረጋገጥ ይችላል” የሚል አጭር ምላሽ ሰጥቶበታል።

ተከላካይ ጠበቆች በበኩላቸው ዐ/ሕግ በጽሑፍ ብቻ በማቅረብ ምስክሮቼ ስጋት አለባቸው በማለት የተከሳሾችን የመከላከል መብት ማጣበብ የለበትም። ስጋት በዝርዝር እና ከምክንያታዊ ጥርጣሬ ውጪ መቅረብ ያለበት ሲሆን ነው የአዋጁንም ዓላማ ሊያሳካ የሚችለው። ስለዚህ ፍ/ቤቱ በማስረጃ ተደግፎ ባልቀረበ የስጋት ጥያቄ የተከሳሾችን ፍትሕ የማግኘት መብት ሊያጣብብ ስለማይገባ ችሎቱ የዐቃቤ ሕግ ጥያቄ ውድቅ እንዲያደርግላቸው ጠይቀዋል።

በመዝገቡ ሦስተኛ ተከሳሽ የሆኑት ቀለብ ሥዩም እየተከራከርን ያለነው የእንስክንድርን ጥያቄ ብቻ አይደለም። የሕዝብ ጥያቄም ይዘን ስለመጣን ፍርድ ቤቱ ግምት ሊሰጠው ይገባል በማለት ዐቃቤ ሕግ ለችሎቱ ሲያስረዳ አንድ ምስክር የግድያ ዛቻ ደርሶበታል ሲል በባልደራስ አመራር ነው? በባልደራስ አባል ነው? ወይስ በባልደራስ ደጋፊ ነው? የሚለውን በግልጽ አብራርቶ ስጋት ያለውን አላቀረበም። ተቀባይነት ሊኖረው አይገባም በማለት፤ "የኛ ክስ ብሔር ከብሔር፣ ሃይማኖት ከሃይማኖት በማጋጨት የ14 ሰዎች ሕይወት ያለፈ ከሆነ ይህ የዳኝነት ሒደት አስተማሪ መሆን ስላለበት በግልጽ ችሎት መሆን አለበት። ሕዝብም ችሎትን መጠርጠር ስለማይኖርበት በግልጽ ችሎት የፍትሕ ስርዓቱ እንዲሠራ አሁንም ፍ/ቤቱን እጠይቃለሁ" ብለዋል። ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኙ ክርክር ውስብስብ ስለሆነ መዝገቡን መርምሮ ብይን ለመስጠት በቂ ግዜ ያስፈልጋል ስለዚህ ቀጠሮ የምንሰጣቹ ከምርጫ በኋላ ነው በማለት ለሰኔ 22፣2013 ተቀጥረዋል።

Add a review

The comment language code.

Restricted HTML

  • Allowed HTML tags: <a href hreflang> <em> <strong> <cite> <blockquote cite> <code> <ul type> <ol start type> <li> <dl> <dt> <dd> <h2 id> <h3 id> <h4 id> <h5 id> <h6 id>
  • Lines and paragraphs break automatically.
  • Web page addresses and email addresses turn into links automatically.