ማረሚያ ቤቱ እነ እስክንድር ነጋን በችሎት ባለማቅረቡ ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠ

ኅዳር 16፣ 2014 - የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ የፀረ ሽብርና ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች ወንጀል ችሎት በእነ እስክንድር ነጋ መዝገብ የቀጠረው ቀሪ ሦስት የዐቃቤ ሕግ ምስክሮች ለማድመጥ ነው።

የማረሚያ ቤት አስተዳደር ተወካይ  የሆኑት ለፍርድ ቤቱ እነ እስክንድር ነጋ ለምን እንዳልቀረቡ በደብዳቤ አቅርበዋል። በተጨማሪም በችሎቱ ጥያቄ መሠረት በቃል አስረድተዋል። "ሰሞኑን ካለው የፀጥታ አኳያ ሸዋ ሮቢት ያሉ እስረኞችን ወደ ዝዋይ ማረሚያ ቤት በመውሰድ እያደራጀን ስለሆነ የማረሚያ ቤት ፖሊሶች በግዳጅ ሥምሪት ላይ ናቸው" ስለሆነም ካለው ነባራዊ ሁኔታ አንፃር ተከሳሾችን ማቅረብ አዳጋች ስለሚሆን  ረጅም ቀጠሮ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።

ተከላካይ ጠበቆች በበኩላቸው ከቂሊንጦ ማረሚያ ሌሎች እስረኞች እየቀረቡ እነ እስክንድር ሳይቀርቡ የሚቀሩበት ወይም ከሌሎች እስረኞች የሚለዩበት ምንም ምክንያት የለም። በሌላ በኩል"ማረሚያ ቤቱ በደብዳቤው ላይ አደራጅቼ እስክጨርስ ግዜ ይሰጠኝ"  ብሏል ግን መቼ አደራጅቶ እንደሚጨርስ ባልታወቀበት ሁኔታ፣ ረጅም ቀጠሮ መስጠት ተከሳሾቹ የዘገየ ፍትሕ እንዲያገኙ መፍረድ ነው ብለዋል።

በተጨማሪም እስክንድር ረጅም ጊዜ ታስረው በቆዩበት ወቅት ብዙ ግዜ ድብደባ ደርሶባቸዋል። ተጨማሪ የቀጠሮ ግዜ መስጠቱ ለተጨማሪ መጉላላት ማጋለጥ ነው፤ በማረሚያ ቤቱ የቀረበው ምክንያት በቂና  ሕጋዊ ባለመሆኑ፣ ውድቅ መደረግ አለበት በማለት አጃቢዎች ተመድበው ተከሳሾች ወደ ፍርድ ቤት መቅረብ እንዲችሉ ችሎቱን ጠይቀዋል።

ፍርድ ቤቱ አስቀድሞ በያዘው ቀጠሮ መሠረት ምስክሮች መገኘታቸውን ለማረጋገጥ ችሎት ቀርበው እንዲያስመዘገቡ ባዘዘው ላይ ዐቃቤ ሕግ ምስክሩ ገብተው የሚታዩ ከሆነ በዝግ ችሎት እንዲሆን ለፍርድ ቤቱ አቤቱታ አቅርቧል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ  በጠበቆች በኩል ባለፈው ችሎት ዐቃቤ ሕግ ለፖሊስ የምስክሮችን አድራሻ እንዲሰጥ እና ፖሊስ መጥሪያ አድርሶ ምስክሮች በፍ/ቤት መጥሪያ እንዲቀርቡ ታዟል፡፡

በመደበኛ የምስክር አሰማም ሒደት ከዚህ ቀደም 6 ምስክሮች ቀርበው በግልጽ ችሎት ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል። በዚህ ጉዳይ ከዚህ በፊት የተከራከርንበት የተዘጋ ጉዳይ ነው፤ ስለዚህ ታዳሚ በተገኘበት በግልጽ ችሎት የምስክር መሰማት ሒደት መቀጠል አለበት ሲሉ ፍርድ ቤቱ በጀመረው አካሄድ እንዲቀጥል ጠበቆች ጠይቀዋል።

የግራ የቀኙን ክርክር የሰማው ፍርድ ቤት የማረሚያ ቤት አስተዳር ኮማንደር አስቻለው መኮንን በነገው እለት ኅዳር 17 ቀን 2014 ፍርድ ቤት በመቅረብ በእነ እስክንድር አቀራረብ ጋር በተያዘ ማብራሪያ እንዲሰጡ ፍ/ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል።

ፍርድ ቤቱ በዐቃቤ ሕግ በኩል ምስክር በዝግ ችሎት ይቅረቡ አቤቱታን ውድቅ በማረድረግ በዕለቱ የቀረቡትን የዐቃቤ ሕግ ምስክር  ወደ ችሎት አዳራሽ እንዲገቡና ሥማቸውን እንዲያስመዘግቡ  አድርጓል።

የዐቃቤ ሕግ ምስክር የሆኑት ጌትነት ተስፋዬ በቀጣይ ቀጠሮ ምንም ዓይነት መጥሪያ ሳይደርሳቸው ወይንም የፍርድ ቤት መጥሪያ ሳይጠብቁ  ከዐቃቤ ሕግ ጋር በስልክ ብቻ በመነጋገር በችሎት እንዲገኙ ጥብቅ ትዕዛዝ ፍርድ ቤቱ  ሰጥቷል።

img

 

img
የፌዴራል ማረሚያ ቤት ያቀረበው እነ እስክንድር ነጋን በሌሎች መዝገቦችም የተከሰሱ እስረኞችን ያላቀረበበትን ምክንያት የገለጸበት ደብዳቤ

 

Add a review

The comment language code.

Restricted HTML

  • Allowed HTML tags: <a href hreflang> <em> <strong> <cite> <blockquote cite> <code> <ul type> <ol start type> <li> <dl> <dt> <dd> <h2 id> <h3 id> <h4 id> <h5 id> <h6 id>
  • Lines and paragraphs break automatically.
  • Web page addresses and email addresses turn into links automatically.