በሁለቱ መዝገቦች የተያዙት ጉዳዮች በድጋሚ ተቀጠሩ

ሐምሌ 30፣ 2013 - የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ የፀረ ሽብረ እና የሕገ መንግሥት ጉዳዮች ወንጀል ችሎት በእነ እስክንድር ነጋ መዝገብ ላይ ከዚህ ቀደም በነበረው ቀጠሮ በግልጽ ችሎት የዐቃቤ ሕግ ምስክሮችን ለመስማት የሰጠው ቀጠሮ ምስክር ሳይሰማ በዐቃቤ ሕግ ይግባኝ አቤቱታ በሰበር ሰሚ ችሎቱ እግድ መጣሉ ይታወሳል

 

የከፍተኛው ፍርድ ቤት የሰበር ውሳኔ ለመጠባበቅ ለሐምሌ 29፣ 2013 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቶ ነበር። ነገር ግን ፍርድ ቤቱ የሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔ ላይ ባለመድረሱ ምክንያት መደበኛውን የተከሳሾቹን ጉዳይ ለመመልከት ለጥቅምት 04፣ 2014 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

 

በሌላ በኩል ችሎቱ በእነ ጃዋር መሐመድ ችሎት ከአራቱ ተከሳሾች ውጪ የቀረቡትን ተከሳሾች ጉዳይ የተመለከተ ሲሆን፣ በቀደመው ቀጠሮ ዐቃቤ ሕግ በምስክሮች አሰማም ሒደት ላይ አሻሽሎ ባቀረበው አቤቱታ ላይ ተከላካይ ጠበቆች የመልስ ጽሑፍ በጽሕፈት ቤት በኩል አቅርበው በችሎት ላይ የቃል ክርክር ለማድረግ ታቅዶ የነበረ ቢሆንም፣ የቃል ክርክር እንደማያስፈልግ ሁለቱም ወገኖች ስለተስማሙበት፤ በቀረበው የጽሑፍ ክርክር ላይ ችሎቱ ብይን ለመስጠት እስከ ሐምሌ 15 ባለው ግዜ  ቀጣይ ቀጠሮ ሰጥቷል። ነገር ግን እስከዛ ድረስ ተሠርቶ የማያልቅ ከሆነ ለጥቅምት 2014 ቀጠሮ ይሰጣል - ብሏል ፍርድ ቤ ።

 

በተያያዘም የምስክር አሰማም ሒደት ላይ የሚሰጠው ብይን በፍቃዳቸው ፍርድ ቤት አንቀርብም ያሉትን ተከሳሾች ጃዋር መሐመድ፣ በቀለ ገርባ፣ ሀምዛ አዳነ እና ደጀኔ ጣፋን እንደማያካትት እና በጠበቆቻቸውም በኩል መወከል እንደማይችሉ ችሎቱ አሳውቋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ እስከ ሐምሌ 15 ባለው ግዜ ቀርበው ክርክር ማረግ ፍላጎት ካላቸው ግን መብታቸው የተጠበቀ እንደሆነ አሳውቀዋል።

 

Add a review

The comment language code.

Restricted HTML

  • Allowed HTML tags: <a href hreflang> <em> <strong> <cite> <blockquote cite> <code> <ul type> <ol start type> <li> <dl> <dt> <dd> <h2 id> <h3 id> <h4 id> <h5 id> <h6 id>
  • Lines and paragraphs break automatically.
  • Web page addresses and email addresses turn into links automatically.