በእነእስክንድር ነጋ መዝገብ የዐቃቤ ሕግ ምስክሮች በግልጽ ችሎት እንዲደመጡ ተወሰነ

ሰኔ 22፣ 2013፤ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ የፀረ ሽብር እና የሕገ መንግሥት ጉዳዮች ወንጀል ችሎት በእነእስክንድር መዝገብ ላይ ዐቃቤ ሕግ አሻሽሎ ያቀረበው አቤቱታን ችሎቱ የተከሳሾችን የመከላከል መብት የሚያጣብብ ስለሆነ በሚል አቤቱታውን ውድቅ በማረግ ምስክሮች በግልጽ ችሎት እንዲመሰክሩ ሲል ብይን ሰቷል።

 

እነእስክንድር ለፍርድ ቤቱ ዐቃቤ ሕግ በድጋሚ ይግባኝ እንዳይጠይቅብን ብለው ለችሎቱ አቤቱታ ቢያቀርቡም ችሎቱ ይህ ጥያቄ እኛን አይመለከተንም ሲል ጥያቄያቸውን ውድቅ አድርጎታል።

 

ተከሳሾቹ ከቃሊቲ ወደ ቂሊንጦ መዛወራቸውን ለችሎቱ በማሳወቅ፣ ፍርድ ቤቱ ከዚህ ቀደም በሰጠው ትዕዛዞች የተዛወሩበት ማረሚያ ላይ ተፈፃሚ እየሆነልን አይደለም፤ በነጻነት ከጠያቂዎቻችን ጋር እንዳናወራም በሁለት ፖሊሶች ታጅበን ነው የምንገናኘው፤ የፀሎት ቦታ እንዲኖረን፣ እንዲሁም ከዚህ በፊት ችሎቱ ፀበል እንዲገባልን ትዕዛዝ ሰጥቶልን የነበረ ቢሆንም እንኳን አሁን ያለንበት ማረሚያ ግን ተፈፃሚ እያደረገልን አይደለም የሚል አቤቱታ አቅርበዋል። ችሎቱ ምስክሮችን ለመስማት ቀጣይ ቀጠሮ ለሐምሌ 8፣ 9 እና 10 ተከታታይ ቀናቶች ሰጥቷል።

 

በምስክሮች አሰማም ሒደት ላይ ከዚህ በፊት የነበሩ ክርክሮችን እዚህ መመልከት ይችላሉ።

 

Add a review

The comment language code.

Restricted HTML

  • Allowed HTML tags: <a href hreflang> <em> <strong> <cite> <blockquote cite> <code> <ul type> <ol start type> <li> <dl> <dt> <dd> <h2 id> <h3 id> <h4 id> <h5 id> <h6 id>
  • Lines and paragraphs break automatically.
  • Web page addresses and email addresses turn into links automatically.