በእነ ዶ/ር ደብረፂዮን ገብረ ሚካኤል መዝገብ የ62 ተከሳሾች የክስ መቃወሚያ በላብቶፕ የያዘው ጠበቃ ዘረሰናይ ወ/ሰንበት ከነላፕቶፑ በመታሰሩ ተቀብለን ለማቅረብ ተለዋጭ ቀጠሮ ይሰጠን ሲሉ ጠበቆች ጠየቁ

ኅዳር 16፣2014 - በእነ ደብረፅዮን መዝገብ የተካተቱት ስብሀት ነጋ፣ ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም፣ ዶ/ር አዲስ ዓለም ባሌማ፣ ዶ/ር አብረሃም ተከስተን፣ ዶ/ር ሰለሞን ኪዳኔ፣ አምባሳደር አባይ ወልዱን ጨምሮ 21 ተከሳሾች ችሎት ያልቀረቡ ሲሆን ማረሚያ ቤቱ የሸዋሮቢት ታራሚዎችን ወደ ዝዋይ በማዘዋወር ሒደት ላይ በመሆኑ ምክንያት ችሎት አለመቅረባቸው በማረሚያ ቤት ጉዳይ አስፈፃሚ በኩል ተገልጿል።

የተከሳሽ ጠበቆችም ማረሚያ ቤቱ ያቀረበው ምክንያት ከተከሳሾች ደኅንነት አንፃር ተገቢ በመሆኑ አንቃወምም ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።

ፍ/ቤቱ በዛሬው ቀጠሮ የተካሳሾን የክስ መቃወሚያ ለመጠባበቅና በፌዴራል ፖሊስ በቁጥጥር ሥር ትገኛለች የተባለችውን የ20ኛ ተከሳሽ የቀድሞ የትግራይ ክልል ገቢዎች ባለሥልጣን ኃላፊ አሰፉ ሌላይ  ፌዴራል ፖሊስ በችሎት እንዲያቀርባት የሰጠውን ትዕዛዝ ለመጠባበቅ እንዲሁም፣ ዐቃቤ ሕግ ዶ/ር ደብረፅዮንን እና ጌታቸው ረዳን ጨምሮ ያልተያዙ ተከሳሾችን የአገር መከላከያ ሠራዊት በልዩ ትዕዛዝ እንዲያቀርባቸው ትዕዛዝ ይሰጥልን ሲል የጠየቀው ጥያቄ ላይ ትዕዛዝ ለመስጠት በተጨማሪም የ44ኛ ተከሳሽ በምርመራ ወቅት የተያዘብኝ ሰነዶች ይመለስልኝ አቤቱታ ላይ ትዕዛዝ ለመስጠት ነበር ዛሬ የተሰየመው። ሆኖም ፍ/ቤቱ ተከሳሾችን ባለማቅረባቸው ምክንያት  በዐቃቤ ሕግ እና በ44ኛ ተከሳሽ የቀረቡት አቤቱታዎች ላይ በቀጣይ ቀጠሮ ተከሳሾቹ ባሉበት ትዕዛዝ እንዲሰጥበት ገልጿል። ዛሬ የቀረበችው 20ኛ ተከሳሽ አሰፉ ሊላይ ጦርነቱ ሲጀምር ትውልድ አገሯ ወልቃይት ሄዳ ታስራ በዋስ እንደወጣች፣ በነሐሴ 11 ቀን 2013 ፌዴራል ፖሊስ በቁጥጥር ሥር ውላ ዛሬ ፍ/ቤት ሳትቀርብ መቆየቷን ገልጻለች። በጉዳዩ ዙሪያ ዐቃቤ ሕግም የታሰረችበትን ምክንያት አላውቅም፣ ሲል ምላሽ መስጠቱን ተከትሎ ፍ/ቤቱም እስካሁን በምን ሁኔታ እንደታሰረች፣ የፌዴራል ፖሊስ ቀርቦ እንዲያስረዳ አዟል። ተከሳሿ በትግራይ ክልል መቀሌ አይደር ክፍለ ከተማ፣ ቀበሌ ዜሮ ሦስት በመንግሥት መሥሪያ ቤት እንደምትኖር እና የክልሉ ገቢዎች ባለሥልጣን ኃላፊ መሆኗን አስመዝግባለች። ፍ/ቤቱም  ፌዴራል ፖሊስ ለተከሳሽ ድርጅቶች መጥሪያ ያልሰጠበትን ምክንያት ቀርቦ እንዲያስረዳ በማዘዝ ትዕዛዝ ያልተሰጠባቸው አቤቱታዎች ላይ ትዕዛዝ ለመስጠትና የተሳሾቹን የክስ መቃወሚያ ለመጠባበቅ ለታኅሣሥ 21 ቀን 2014 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

Add a review

The comment language code.

Restricted HTML

  • Allowed HTML tags: <a href hreflang> <em> <strong> <cite> <blockquote cite> <code> <ul type> <ol start type> <li> <dl> <dt> <dd> <h2 id> <h3 id> <h4 id> <h5 id> <h6 id>
  • Lines and paragraphs break automatically.
  • Web page addresses and email addresses turn into links automatically.