ካርድ የሁለት ቀናት የዲጂታል ደኅንነት ሥልጠና ሰጠ

FB_event

ካርድ፣ ከፌስቡክ ጋር በመተባበር የካቲት 17 እና 18፣ 2012 በኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል ባዘጋጀው የሁለት ቀናት ሥልጠና ላይ ከአዲስ አበባ እና ክልሎች የመጡ 24 የሲቪል ማኅበራት ተወካዮች፣ ጋዜጠኞች እና የመብት ተሟጋች ግለሰቦች ተገኙ። ሥልጠናው የዲጂታል ደኅንነትና የዲጂታል አክቲቪዝም አቅምን ማጎልበት ላይ የሚያጠነጥን ነበር። 

የዲጂታል ደኅንነት ሥልጠናውን የሰጡት የካርድ የፕሮግራም ዳይሬክተር አጥናፉ ብርሃኔ እና ዩጋንዳዊው የዲጂታል ደኅንነት አሠልጣኝ ጎሌ አንድሩ ሲሆኑ፣ ሐሰተኛ መረጃዎችን መለየት እና መዋጋት እንዲሁም የዲጂታል አጠቃቀም ችሎታን ማሳደግ ክህሎት ላይ የዲጂታል ፓርትነርስ ግሎባል እና የፌስቡክ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።

ሥልጠናው ካርድ ከፌስቡክ ጋር በመተባበር ከሚያዘጋጃቸው መርሐ ግብሮች ውስጥ የመጀመሪያው ነው።

Add a review

The comment language code.

Restricted HTML

  • Allowed HTML tags: <a href hreflang> <em> <strong> <cite> <blockquote cite> <code> <ul type> <ol start type> <li> <dl> <dt> <dd> <h2 id> <h3 id> <h4 id> <h5 id> <h6 id>
  • Lines and paragraphs break automatically.
  • Web page addresses and email addresses turn into links automatically.