ካርድ የተዛቡ መረጃዎች እና የጥላቻ ንግግር በቀጣዩ ምርጫ ላይ የሚያጠላውን አደጋ የሚገልጽ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጠ
ካርድ በቀጣይ ምርጫ 2012 የጥላቻ ንግግርና የተዛቡ መረጃዎች ሊያጠሉ ስለሚችሉት አደጋ፣ ጥር 21፣ 2012 ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል። ካርድ ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ለማካሔድ የጥላቻ ንግግርና የተዛቡ መረጃዎች ስርጭትን መከላከል ከፍተኛ ትኩረት የሚገባው ጉዳይ መሆኑን በመግለጫው ላይ ገልጿል።
ላለፉት ስድስት ወራት፣ ካርድ የሐሰተኛ መረጃዎችን ስርጭት እና የጥላቻ ንግግሮችን በተመለከተ ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ቅኝት ሲያደርግ እንደነበረ በመግለጫው ላይ የተገለጸ ሲሆን፣ የሐሰተኛ መረጃዎች እና የጥላቻ ንግግሮችን መቀነስ ካልተቻለ ዜጎች በተሳሳተ መረጃ የተሳሳተ ምርጫ እንዲያደርጉ ሊገደዱ ከመቻላቸውም በላይ ግጭት ሊቀሰቀስ ይችላል የሚል ስጋት እንዳለው የካርድ መግለጫ ያትታል።
ካርድ ይህንን ለመከላከል ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪ ያቀረበ ሲሆን፣
- የመንግሥት ግልጽነት እና ተጠያቂነት፣
- የብዙኀን መገናኛዎች ሐቅ የማረጋገጥ ሥራ እና
- የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች የብዙኀን መገናኛ ግንዛቤ ማሳደግ ሥራዎች ዋና ዋና መሆናቸው ተጠቅሷል።
ሙሉ መግለጫው እዚህ ይገኛል።
ፋና ቴሌቪዥን ስለ ጋዜጣዊ መግለጫው የሠራውን ዘገባ ከታች ይመልከቱ።
Add a review