በእነ እስክንድር ነጋ መዝገብ የዐቃቤ ሕግ ምስክሮች ለሁለተኛ ቀን ተደመጡ
ጥቅምት 15፣ 2014 - የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አንደኛ የፀረ ሽብር እና ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች ችሎት ከመሰየሙ በፊት የእስክንድር ነጋን አቤቱታ ተቀብሏል።
በመዝገቡ የመጀመሪያ ተከሳሽ የሆኑት እስክንድር ነጋ “በዘረፋ ወንጀል ተጠርጥሮ በታሰረ ግለሰብ ተደብድቤ የግራ አውራ ጣቴ ተሰብሮ፣ ለ6 ወር የሚቆይ ጄሶ ታስሮልኛል” በማለት ጉዳት የደረሰባቸውን እግር ለችሎቱ አሳይተዋል። “ድርጊቱ ደግሞ ሆን ተብሎ ስፖርት በምሠራበት ወቅት ነው የተፈፀመብኝ፣ ስለዚህ ከማረሚያ ቤቱ አሠራር ውጪ፣ እኔ በሌለሁበት ግለሰቡን ወደ ዞኑ የመለሱት ኃላፊዎች ላይ፣ ፖሊስ መጥቶ ቃሌን መስጠት እፈልጋለሁ” ብለዋል። በተጨማሪም ዐቃቤ ሕግ ጉዳዩን ይዞ ያጣራልኝ ሲሉ አቤቱታ ለችሎቱ አሰምተዋል። ችሎቱም አቤቱታቸውን አዳምጦ በቀጥታ ምስክር ወደማድመጥ ገብቷል።
የማጣሪያ ጥያቄ በዐቃቤያን በኩል ለአንደኛ ምስክር ቀርቧል። በስንት እንደታሰሩ እና እንደተፈቱ እና ከሕዝባዊ መብቶቻቸው ታግደው እንደሆነ እና ከተሰጣቸው ተልዕኮ የተሳካ ከነበረ ተብሎ በተጠየቁት መሰረት ምስክሩም (ፋንታሁን) የታሰሩት ሐምሌ 1992 ታስረው ሕዳር 2011 እንደተፈቱ በመግለጽ፣ ከተሰጣቸው ተልዕኮ ቤተ ክርስቲያን ማቃጠል እና መስኪድ የማቃጠል ተልዕኮ የትኛውንም አለማሳካታቸውን እና ከየትኛውም ሕዝባዊ መብታቸው አለመታገዳቸውም አያይዘው መልሰዋል።
በችሎቱ በኩልም የማጣሪያ ጥያቄ ቀርቦላቸው አንደኛ ምስክር ምላሽ ሰተዋል፤ የታሰሩበት ቀን ሲጠየቁ ምስክር “በሐምሌ ወር 1991” ብለዋል፤ ፍርድ ቤቱም “አቶ አሸናፊ ከአቶ እስክንድር ጋር በሚያስተዋውቅዎት ወቅት ለእርስዎ አዲስ የሆነ ጉዳይ ሲነገርዎት እንዴት ዓላማውን ሳይጠይቁ ቀሩ?” ብሎ ሲጠይቅ ምስክሩ “በወቅቱ መጠየቅ ስላልፈለኩ” የሚል ምላሽ ሰጥተውበታል።
ፍርድ ቤቱ ምስክሩን የተጠቀሱት የእምነት ተቋማት ቦታ የት ነው? ምስክር አቡነ አረጋዊ ቤተክርስቲያን አለርት ጋር መስኪድ ተብሎ የተጠራው አባባ ተብሎ የሚጠራ ነው ነገር ግን ሀይማኖታዊ ትምህርት ቤት መሆኑን ገልጸዋል። ፣ይህን ጉዳይ አላማውን ካወቁ በኃላ ስላልደገፉት መተዎን አስረድተዋል ነገር ግን ሪፖርት ለማረግ የዘገዩበት ምክንያት ምንድነው? ምስክር እጅ ከፍንጅ ለማሲያዝየሚል ምላሽ ሰተውበታል፤የመሳሪያ ስልጠናስ ወስዳችኃል? አልወሰድንም ብለዋል።
ችሎቱ ለምስክሩ በወቅቱ መሣሪያ እና ገንዘብ ፈልገው እንደነበር ገልጸዋል፣ አንደኛ ተከሳሽ ስለጥቅማ ጥቅም የተናገሩት ነበረ ወይ ብለው ጠይቀው ምስክሩ እንዳልነበረ ምላሽ ሰተውበታል። ፍርድ ቤቱም አያይዞ “በደንብ ከማያቁት ግለሰብ ጋር ጉዞ ሲያደርጉ ወዴት እንደሚሔዱ ለምን አልጠየቁም?” ያለ ሲሆን ምስክሩም “ዓላማችሁ አንድ ነው ስለተባልኩ አልጠየኩም” የሚል ምላሽ ሰተዋል።
በመጨረሻም ችሎቱ ለምስክሩ የሚደርሳቸው ትዕዛዝ ከእስክንድር መሆኑን እንዴት እንደ አወቁ፣ በተጨማሪም ሌሎች ተከሳሾችን ያውቋቸው እንደሆነ ጠይቋል። ምስክሩም ሌሎቹን እንደማያውቋቸው እና ትዕዛዙ ከእስክንድር መሆኑን አቶ አሸናፊ በስልክ በሚያወሩበት ወቅት በሙሉ አቶ እስክንድር ናቸው ስለሚሏቸው እንደሆነ ብቻ ለችሎቱ ገልጸዋል።
ከሰዓት በዋለው ችሎት የዐቃቤ ሕግ ሁለተኛ ምስክር በአንደኛ ተከሳስሽ ላይ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል።
ሁለተኛ ምስክር ወ/ሮ መንበረ በቀለ፣ በልደታ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 07 የቤቶች አስተዳደር እንደነበሩ አሁን ላይ ደሞ ወረዳ 06 ፐፕሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት አስተዳደር እንደሚሰሩ ገልጸዋል።
በ2012 ሚያዚያ ወር አካባቢ የአቶ ፋንታሁን ባለቤት ነኝ ያለች ሴትዮ ቢሮዬ መጥታ “እስክንድር (ባልደራስ) ሊያስገድልሽ ስለሆነ እሱ (ፋንታሁን) ሳይመጣ ከቢሮ እንዳትወጪ ብላ መልዕክት ነገረችኝ። ከዛ በኋላ እሱ መቶ ባልደራሶች ያደራጀነውን አባል እየበተነችብን ብለው ሊያስገድሉኝ እንደሚፈልጉ ነግሮኛል። በተጨማሪም የሥራ መውጫ እና መግቢያ ሰዓቴን መቀየር እንዳለብኝ በመንገር በታክሲ እስከ ግማሽ መንገድ አብረን ሔደን ስልኩን ተቀብዬ ተለያይተናል። በሰዓቱም ለፖሊስ ማሳወቅ እንደሌለብኝ ነግሮኛል። ያሰብኩት ነገር ስላለ ታበላሺብኛለሽ ስላለኝ ወደ ፖሊስ አልሄድኩም” ብለዋል።
ዐቃቤ ሕግ “ሥራዎት ከፓርቲው ጋር ያገናኞታል? የደረሰቦትስ ነገር አለ?” ሲል ላቀረበው ጥያቄ ምስክሩ “የብልጽግና አባል ስለሆንኩ፣ አባል መለምለው ከተለያዩ ፓርቲም ወደ እኛ ያመጣናቸው አሉ” ካሉ በኋላ ከዚህ ውጪ ግን ሌላ የሚያገናኛቸው ነገር እንደሌለ እና ሊገደሉ ነው የሚል መረጃ በደረሳቸው ስጋት እን እና መውጫ መግቢያ ሰዓት እንደቀየሩ ገልጸዋል።
በጠበቆች በኩል ዕድሚያቸውን በሚመለከት ለችሎቱ 37 ማለታቸውን በማስታወስ እና የተወለዱበትን ጊዜ እንዲነግሯቸው ተጠይቀው፣ እንደማያውቁት መልሰዋል። ነገር ግን “መታወቂያቸው ላይ ባለው የትውልድ ዓመት 40 እንደሚሆናቸው ነው ያየነው” ሲሉ ምስክሯም “አስተውዬ አይቼ አልተቀበልኳቸውም” ብለዋል።
አቶ ፋንታሁንን ከዛ በፊት ያውቋቸው እንደነበር፣ ጉዳዩን በሚነግሯቸው ወቅት የሥራ ባልደረቦቻቸው ሰምተው እንደነበር፣ ምስክሯ በመስቀለኛ ጥያቄ ተጠይቀው፣ ፋንታሁን መታወቂያ ለመውሰድ በሚመላለሱበት ወቅት በዓይን እንደሚተዋወቁ እና ከሥራ ባልደረቦቻቸው ማንም እንዳልሰማ ምላሽ ሰጥተዋል።
በመጨረሻም በማጣሪያ ጥያቄ ምስክሯ ከእስክንድ ውጪ የተነገራቸው ሥም እንደሌለ እና ፖሊስ ኮሚሽን ለማመልከት ከወር በኋላ የሔዱት ፋንታሁን ስለተተኮሰበት እንደነበር፣ በተጨማሪም ቃል ለመስጠት እንደነበር፤ ከዐቃቤ ሕግ ቢሮ፣ ከማጋረጃ ጀርባ እንደሚመሰክሩ ተደውሎ እንደተነገራቸው መስክረዋል።
የአቶ እስክንድር ድብደባ በሚመለከት ችሎቱ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የሰብዓዊ ጥሰት መድረሱን መርምሮ ያቅርብልን፤ በተጨማሪም የፌደራል ወንጀል ምርመራ ጉዳዩን አጣርቶ ወንጀል መፈፀሙን ለሚመለከተው አካል ያቅርብ ብሏል። በተያያዘም የዘመድ ጥየቃ ሰዓት በሚመለከት በአቶ እስክንድር የቀን ምርጫ፣ ሰኞ ከሰዓት ለ30 ደቂቃ ማግኘት እንዲችሉ ፍርድ ቤቱ ፈቅዷል። ነገር ግን በማን ስልክ የሚለውን ማረሚያ ቤቱ አስተያየት እንዲሰጥበት ትዕዛዝ ተሰጥቷል።
የአቶ ስንታየሁ ቸኮል የሕክምና ጥያቄ በሚመለከት ማረሚያ ቤቱ፤ አስቀድሞ ችሎቱን ሳይሆን ማረሚያ ቤቱን ነበር መጠየቅ የነበረበት የሚል ምላሽ ሰተውበታል።
አቶ እስክንድር ደጋፊዎቻቸው ላይ በደረሰው እስራት ምክንያት አቤቱታ ያቀረቡ ሲሆን፣ ፍርድ ቤቱ “ከዚህ ችሎት እርምት እና ተግሳጽ ተሰቷቸዋል፤ ጉዳዩ እልባት አግኝቶ ወጥተዋል። ነገር ግን ከችሎቱ ውጪ ለተፈፀመው ድርጊት፣ አቤቱታ ማቅረብ ያለባችሁ ከችሎቱ ውጪ ላለ አካል ነው ማቅረብ ያለችሁ” ብሏል።
በተያያዘ ዜና አርባዎቹ ታሳሪዎች አመሻሹ ላይ እንደተፈቱ ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ በፌስቡክ ገጹ አመሻሹ ላይ ገልጿል።
Add a review