Skip to main content

የሥልጠና ምዝገባ ጥሪ ለሪፖርተሮች ፣ ለሚዲያ አመራሮች እንዲሁም ለአዘጋጆች

የመብቶችና ዲሞክራሲ ዕድገት ማዕከል (ካርድ) በአዋጅ ቁጥር 1113/2011 በሲቪል ማኅበራት ድርጅቶች ኤጀንሲ ምዝገባ ቁጥር 4307 የተመዘገበ ቦርድ-መር፣ አገር በቀል፣ መንግሥታዊ ያልሆነ እና ለትርፍ ያልተቋቋመ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅት ነው። ካርድ በሰብዓዊ መብቶች እሴቶች ላይ የቆመ ዴሞክራሲያዊ ባሕል ያበበባት ኢትዮጵያን ማየት ራዕይ አድርጎ ሰንቆ፥የኢትዮጵያ ዜጎች እና የዜጎች ማኅበራት ለሰብዓዊ መብቶች መከበር በመሟገት ዲሞክራሲያዊ አስተዳደር እንዲያሰፍኑ የሚያስችላቸውን የአቅም ግንባታ ማድረግ ተልዕኮ በማንገብ እየሠራ የሚገኝ ድርጅት ነው። 

ካርድ ከፈረንሳይ ልማት ኤጀንሲ (AFD) ጋር በመተባበር የሰብአዊ መብቶች አገናዛቢ አዘጋገብ ላይ ለጋዜጠኞች፣ ለሚዲያ አመራሮች እንዲሁም ለአዘጋጆች የሁለት ቀናት የሥልጠና ለመስጠት ዝግጅቱን አጠናቋል። የዚህ ሥጠልጠና ተሳታፊ መሆን የምትፈልጉ የሚዲያ አመራሮች፣ አዘጋጆች እና ጋዜጠኞች ይህንን ቅጽ በመሙላት በሥልጠናው ለመሳተፍ እንድታመለክቱ እንጋብዛችኋለን። 

ለተጨማሪ መረጃ ወይንም ጥያቄ በስልክ ቁጥር +251116-67-18-70 መደወል አልያም በinfo@cardethorg የኢሜል መልዕክት በመፃፍ መረጃ ማግኘት እንደምትችሉ እናሳውቃለን።

Share this post

Comments (0)

Add new comment

The comment language code.

Restricted HTML

  • Allowed HTML tags: <a href hreflang> <em> <strong> <cite> <blockquote cite> <code> <ul type> <ol start type> <li> <dl> <dt> <dd> <h2 id> <h3 id> <h4 id> <h5 id> <h6 id>
  • Lines and paragraphs break automatically.
  • Web page addresses and email addresses turn into links automatically.