የካርድ አውራምባ ጠቋሚ 2015

የመብቶች እና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል (ካርድ) በዓይነቱ የመጀመሪያው የሆነውን አውራምባ ጠቋሚ 2015 ይፋ አደረገ። ይህ የኢትዮጵያ የፌዴሬሽን አባላትን የዴሞክራሲያዊነት ሒደት የሚመዘንበት አውራምባ ጠቋሚ የተባለ ሪፖርት ኢትዮጵያ በሰብዓዊ መብቶች እሴቶች ላይ ያበበ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታን በእውቀት እንድታደርግ ያግዛል ተብሎ በማዕከሉ ተስፋ ተጥሎበታል። 

አውራምባ ጠቋሚ ሥያሜውን ያገኘው በ1970ዎቹ በደቡብ ጎንደር ዞን ፎገራ ወረዳ ከተመሰረተው እና ከ400 በላይ ነዋሪዎች ካፈራው የአውራምባ ማኅበረሰብ ነው። አውራምባ አመራሩ በፈቃዳቸው በተሰባሰቡ ሰዎች ፍላጎት ሆነ ተብሎ የተቀረፀ በመሆኑ ጠቋሚው ለሚያራምደው ዴሞክራሲያዊነትን በብዙኃን ይሁንታ የመገንባት ሒደት ምሣሌ ይሆናል ተብሎ ታምኗል። አውራምባ ጠቋሚ በ2015 የዴሞክራሲያዊነት ሒደቱ አዎንታዊ  ማሻሻያ ማሳየት አለማሳየቱን መመዘን ላይ ያተኮረ ሲሆን፣ የአምስት ክልላዊ መስተዳድሮችን እንዲሁም የአዲስ አበባ ከተማን ዓመታዊ የዴሞክራሲያዊነት ሒደት ገምግሟል። ምዘናው አስቀድሞ የተወሰነ ጥናታዊ ሥነ ዘዴን በመጠቀም የፖለቲካ ብዝኃነት፣ የኅዳጣን ጥበቃ፣ የዜጎች ነጻነት እና የመሳሰሉትን የዴሞክራሲያዊነት ባሕሪዎች መሠረት አድርጎ መስተዳድሮቹን በ25 መገለጫዎች መዝኗቸዋል። 

ሙሉ ሪፖርቱን እዚህ ያግኙ

Add a review

The comment language code.

Restricted HTML

  • Allowed HTML tags: <a href hreflang> <em> <strong> <cite> <blockquote cite> <code> <ul type> <ol start type> <li> <dl> <dt> <dd> <h2 id> <h3 id> <h4 id> <h5 id> <h6 id>
  • Lines and paragraphs break automatically.
  • Web page addresses and email addresses turn into links automatically.