የክልሎችን አስተዳደር ለመመዘን የሚዘጋጁ ወርክሾፖች ላይ ለመሳተፍ የሚያስችል ምዝገባ ለማድረግ የወጣ ጥሪ

የመብቶች እና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል (ካርድ) በተለያዩ የማኅበረ-ፖለቲካዊ ዘርፎች የሠለጠኑ ባለሙያዎች ተሳትፎ የክልሎች አስተዳደር ከዴሞክራሲያዊ መርሖዎች አንፃር የሚመዘንበትን ሒደት አመቻችቷል። የምዘናው ዋነኛ አካል ባለሙያዎች የሚሳተፉበት ወርክሾፕ ሲሆን፣ በወርክሾፑ የሚሳተፉት ባለሙያዎች በሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች ላይ እየተወያዩ ምዘናቸውን ይሰጣሉ። በእነዚህ ወርክሾፖች የሚሳተፉ ባለሙያዎች የዕለት ወጪ አበል ይታሰብላቸዋል። 

የምዘና ሒደቱ ላይ የሚሳተፉ ባለሙያዎች የሚከተሉት ሙያዊ ብቃቶች ሊኖሯቸው ይገባል፤

  • በአንድ ክልል ወይም ክልሎች ውስጥ ያለውን አስተዳደራዊ ሁኔታ በቅርብ የሚያውቁ እና የሚከታተሉ፣ 

  • በሲቪል ነጻነት፣ በምርጫ እና ፖለቲካዊ ብዝኃነት፣ በማኅበረ-ፖለቲካዊ መብቶች፣ በመንግሥት አገልግሎት ቀልጣፋነት፣ በአናሳ ቁጥር ያላቸው ሕዝቦች ጥበቃ፣ ወይም በሥልጣን ቁጥጥር እና ሚዛን ርዕሰ ጉዳዮች የተለየ ትኩረት እና ዕውቀት ያላቸው፣

  • ለጉዳዩ ረብነት ባለው የማኅበራዊ ሳይንስ ጥናት ሁለተኛ ዲግሪ ወይም ከዚያ በላይ ያለቸው፣ 

የተመረጡ አመልካቾች 30 ጥያቄዎች ላይ በመወያየት መጠይቅ የሚሞሉበት ወርክሾፕ ላይ ለአንድ ቀን ይሳተፋሉ። ተሳታፊዎች በቀን 3000 ብር አበል ይታሰብላቸዋል። አንዳንድ ባለሙያዎች በትምህርት እና ልምዳቸው መሠረት በበርካታ ወርክሾፖች ላይ እንዲሳተፉ ሊመረጡ ይችላሉ። 

በእነዚህ ወርክሾፕ ላይ ለመሳተፍ ይህንን ሊንክ ክሊክ በማድረግ ፎርሙን ይሙሉ።

የማመልከቻው ጊዜ መጠናቀቂያ ሐምሌ 29፣ 2015 ነው።

Add a review

The comment language code.

Restricted HTML

  • Allowed HTML tags: <a href hreflang> <em> <strong> <cite> <blockquote cite> <code> <ul type> <ol start type> <li> <dl> <dt> <dd> <h2 id> <h3 id> <h4 id> <h5 id> <h6 id>
  • Lines and paragraphs break automatically.
  • Web page addresses and email addresses turn into links automatically.